Apocalipse 16
መጽሐፍ ቅዱስ · Toque num versículo para ver as referências cruzadas.
1ለሰባቱም መላእክት። ሄዳችሁ የእግዚአብሔርን ቁጣ ጽዋዎች በምድር ውስጥ አፍስሱ የሚል ታላቅ ድምፅ ከመቅደሱ ሰማሁ። 2ፊተኛውም ሄዶ ጽዋውን በምድር ውስጥ አፈሰሰ፤ የአውሬውም ምልክት ባለባቸው ለምስሉም በሚሰግዱ ሰዎች ክፉኛ የሚነዘንዝ ቍስል ሆነባቸው። 3ሁለተኛውም ጽዋውን በባሕር ውስጥ አፈሰሰ፤ እንደ ሞተም ሰው ደም ሆነ፥ በባሕርም ከሚኖሩት ሕይወት ያለበት ነፍስ ሁሉ ሞተ። 4ሦስተኛውም ጽዋውን በወንዞችና በውኃ ምንጮች ውስጥ አፈሰሰ፤ እነርሱም ደም ሆኑ። 5የውኃውም መልአክ። ያለህና የነበርህ ጌታ ሆይ፥ ቅዱስ ሆይ፥ እንዲህ ስለፈረድህ ጻድቅ ነህ፤ 6የቅዱሳንና የነቢያትን ደም ስላፈሰሱ ደምን ደግሞ አጠጥተሃቸዋል፥ የሚገባቸው ነውና ብሎ ሲናገር ሰማሁ። 7ከመሰዊያውም። አዎን፥ ሁሉን የምትገዛ ጌታ አምላክ ሆይ፥ ፍርዶችህ እውነትና ጽድቅ ናቸው ብሎ ሲናገር ሰማሁ። 8አራተኛውም ጽዋውን በፀሐይ ላይ አፈሰሰ፤ ሰዎችንም በእሳት ልታቃጥል ተሰጣት። 9ሰዎችም በታላቅ ትኵሳት ተቃጠሉ፥ በነዚህም መቅሠፍቶች ላይ ሥልጣን ያለውን የእግዚአብሔርን ስም ተሳደቡ፥ ክብርንም እንዲሰጡት ንስሐ አልገቡም። 10አምስተኛውም ጽዋውን በአውሬው ዙፋን ላይ አፈሰሰ፤ መንግሥቱም ጨለማ ሆነች ከስቃይም የተነሳ መላሶቻቸውን ያኝኩ ነበር፥ 11ከስቃያቸውና ከቍስላቸውም የተነሳ የሰማይን አምላክ ተሳደቡ፥ ከስራቸውም ንስሐ አልገቡም። 12ስድስተኛውም ጽዋውን በታላቁ ወንዝ በኤፍራጥስ ላይ አፈሰሰ፤ ከፀሐይም መውጫ ለሚመጡ ነገሥታት መንገድ እንዲሰናዳላቸው ውኃው ደረቀ። 13ከዘንዶውም አፍና ከአውሬው አፍ ከሐሰተኛውም ነቢይ አፍ ጓጕንቸሮች የሚመስሉ ሦስት ርኵሳን መናፍስት ሲወጡ አየሁ፤ 14ምልክት እያደረጉ የአጋንንት መናፍስት ናቸውና፥ በታላቁም ሁሉን በሚገዛ በእግዚአብሔር ቀን ወደ ሚሆነው ጦር እንዲያስከትቱአቸው ወደ ዓለም ሁሉ ነገሥታት ይወጣሉ። 15እነሆ፥ እንደ ሌባ ሆኜ እመጣለሁ፤ ራቁቱን እንዳይሄድ እፍረቱንም እንዳያዩ ነቅቶ ልብሱን የሚጠብቅ ብፁዕ ነው። 16በዕብራይስጥም አርማጌዶን ወደሚባል ስፍራ እስከተቱአቸው። 17ሰባተኛውም ጽዋውን በአየር ውስጥ አፈሰሰ፤ ከመቅደሱም ውስጥ። ተፈጽሞአል የሚል ታላቅ ድምጽ ከዙፋኑ ወጣ። 18መብረቅና ድምጽም ነጎድጓድም ሆኑ፥ ትልቅም የምድር መናወጥ ሆነ፤ ሰው በምድር ከተፈጠረ ጀምሮ እንዲህ ያለ ታላቅ መናውጥ ከቶ አልነበረም፤ ከሁሉ በለጠ። 19ታላቂቱም ከተማ በሦስት ተከፋፈለች፥ የአሕዛብም ከተማዎች ወደቁ። ታላቂቱም ባቢሎን የብርቱ ቍጣው ወይን ጠጅ የሞላበትን ጽዋ እንዲሰጣት በእግዚአብሔር ፊት ታሰበች። 20ደሴቶችም ሁሉ ሸሹ ተራራዎችም አልተገኙም። 21በሚዛንም አንድ ታላንት*ፍ1* የሚያህል ታላቅ በረዶ በሰዎች ላይ ከሰማይ ወረደባቸው፤ ሰዎቹም ከበረዶው መቅሰፍት የተነሳ እግዚአብሔርን ተሳደቡ፥ መቅሰፍቱ እጅግ ታላቅ ነውና።

Você sabia?
As sete taças da ira
- O nome Armagedom aparece somente em Apocalipse 16:16, onde os reis se reúnem para a batalha; a Revised Version inglesa grafa Har-Magedon. O Easton's Bible Dictionary (1897) diz que a palavra significa propriamente monte de Megido e a trata como nome simbólico desse campo de batalha, imagem sugerida pelo grande campo de batalha do Antigo Testamento, a planície de Esdrelão.Fontes: Armageddon · o próprio texto bíblico
- A sexta taça é derramada sobre o grande rio Eufrates, e a água seca para preparar o caminho dos reis do Oriente. O Easton's Bible Dictionary deriva o nome grego Eufrates do persa Ufratush, com o sentido de água doce, e observa que o nome assírio significa a corrente ou a grande corrente. Na Bíblia, esse rio muitas vezes é chamado simplesmente de o rio (Êxodo 23:31) ou de o grande rio (Deuteronômio 1:7).Fontes: Euphrates · o próprio texto bíblico
- Quando a sétima taça é derramada, o texto diz que Deus se lembrou da grande Babilônia. O Easton's Bible Dictionary identifica Babilônia como a forma grega de Babel, a partir do nome semítico Babilu, a Porta de Deus, cidade que ficava às margens do Eufrates, cerca de duzentas milhas acima do ponto em que o rio encontra o Tigre.Fontes: Babylon · o próprio texto bíblico
Notas escritas com auxílio de IA a partir de fontes abertas (Theographic Bible Metadata, CC BY-SA 4.0; Easton’s Bible Dictionary, domínio público) e revisadas antes de publicar.
Lugares deste capítulo
- East · Hoje: region around Amman · 31.955, 35.934 · versículo 12
- Euphrates · Hoje: Euphrates River · 31.004, 47.442 · versículo 12
- Babylon · Hoje: Rome · 41.892, 12.485 · versículo 19
Só aparecem lugares com identificação de alta confiança (90% ou mais segundo as fontes acadêmicas reunidas pelo OpenBible). Mapa da época: DARE (Digital Atlas of the Roman Empire), CC BY 4.0; mapa atual: © colaboradores do OpenStreetMap; lugares: OpenBible.info (CC BY 4.0).
Créditos e licença desta tradução
መጽሐፍ ቅዱስ The New Testament in the Amharic language of Ethiopia copyright © 1962, 2003 United Bible Societies Language: አማርኛ (Amharic) Amharic NT Revised Amharic Bible in XML (2003). Printed version by United Bible Societies (C)1962. E-Text in transliterated ASCII format by Lapsley/Brooks Foundation 1994. Unicode UTF-8 transformation and XML-tagging by Dirk Röckmann 2003 ( www.nt-text.net ). With kind permission of the Bible Society of Ethiopia. Every non-commercial work using this data in any form must fully include this copyright statement! Every commercial use of parts or the complete data in any form needs written permission of the Bible Society of Ethiopia! 2014-09-09
Fonte: http://ebible.org/amh/ · eBible.org