Nations Bible

Marcos 7

መጽሐፍ ቅዱስ · Toque num versículo para ver as referências cruzadas.

1ፈሪሳውያንና ከጻፎች ወገን ከኢየሩሳሌም የመጡትም ወደ እርሱ ተሰበሰቡ። 2ከደቀ መዛሙርቱም አንዳንድ በርኵስ ማለት ባልታጠበ እጅ እንጀራ ሲበሉ አዩ። 3ፈሪሳውያንና አይሁድም ሁሉ የሽማግሎችን ወግ ሲጠብቁ እጃቸውን ደኅና አድርገው ሳይታጠቡ አይበሉምና፥ 4ከገበያም ተመልሰው ካልታጠቡ አይበሉም፥ ጽዋንም ማድጋንም የናስ ዕቃንም አልጋንም እንደ ማጠብ ሌላ ነገር ሊጠብቁት የተቀበሉት ብዙ አለ። 5ፈሪሳውያንም ጻፎችም። ደቀ መዛሙርትህ እንደ ሽማግሌዎች ወግ ስለ ምን አይሄዱም? ነገር ግን እጃቸውን ሳይታጠቡ እንጀራ ይበላሉ ብለው ጠየቁት። 6እርሱ ግን እንዲህ አላቸው። ኢሳይያስ ስለ እናንተ ስለ ግብዞች። ይህ ሕዝብ በከንፈሩ ያከብረኛል ልቡ ግን ከእኔ በጣም የራቀ ነው፤ 7የሰውም ሥርዓት የሆነ ትምህርት እያስተማሩ በከንቱ ያመልኩኛል ተብሎ እንደ ተጻፈ በእውነት ትንቢት ተናገረ። 8የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ትታችሁ ጽዋን ማድጋንም እንደ ማጠብ የሰውን ወግ ትጠብቃላችሁ፥ ይህንም የመሰለ ብዙ ሌላ ነገር ታደርጋላችሁ። 9እንዲህም አላቸው። ወጋችሁን ትጠብቁ ዘንድ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ እጅግ ንቃችኋል። 10ሙሴ። አባትህንና እናትህን አክብር፤ ደግሞ። አባቱን ወይም እናቱን የሰደበ ፈጽሞ ይሙት ብሎአልና። 11እናንተ ግን ትላላችሁ። ሰው አባቱን ወይም እናቱን። ከእኔ የምትጠቀምበት ነገር ሁሉ ቍርባን ማለት መባ ነው ቢል፥ 12ለአባቱና ለእናቱ ምንም እንኳ ሊያደርግ ወደ ፊት አትፈቅዱለትም፤ 13ባስተላለፋችሁትም ወግ የእግዚአብሔርን ቃል ትሽራላችሁ፤ እንደዚሁም ይህን የሚመስል ብዙ ነገር ታደርጋላችሁ። 14ደግሞም ሕዝቡን ጠርቶ። ሁላችሁ እኔን ስሙ አስተውሉም። 15ከሰው የሚወጡት ሰውን የሚያረክሱ ናቸው እንጂ ከሰው ውጭ የሚገባውስ ሊያረክሰው የሚችል ምንም የለም። 16የሚሰማ ጆሮ ያለው ቢኖር ይስማ አላቸው። 17ከሕዝቡ ዘንድ ወደ ቤት ከገባ በኋላ ደቀ መዛሙርቱ ምሳሌውን ጠየቁት። 18እርሱም። እናንተ ደግሞ እንደዚህ የማታስተውሉ ናችሁን? ከውጭ ወደ ሰው የሚገባ ሊያረክሰው ምንም እንዳይችል አትመለከቱምን? 19ወደ ሆድ ገብቶ ወደ እዳሪ ይወጣል እንጂ ወደ ልብ አይገባምና፤ መብልን ሁሉ እያጠራ አላቸው። 20እርሱም አለ። ከሰው የሚወጣው ሰውን የሚያረክስ ያ ነው። 21ከውስጥ ከሰው ልብ የሚወጣ ክፉ አሳብ፥ 22ዝሙት፥ መስረቅ፥ መግደል፥ ምንዝርነት፥ መጐምጀት፥ ክፋት፥ ተንኰል፥ መዳራት፥ ምቀኝነት፥ ስድብ፥ ትዕቢት፥ ስንፍና ናቸውና፤ 23ይህ ክፉው ሁሉ ከውስጥ ይወጣል ሰውን ያረክሰዋል። 24ከዚያም ተነሥቶ ወደ ጢሮስና ወደ ሲዶና አገር ሄደ። ወደ ቤትም ገብቶ ማንም እንዳያውቅበት ወደደ ሊሰወርም አልተቻለውም፤ 25ወዲያው ግን ታናሺቱ ልጅዋ ርኵስ መንፈስ ያደረባት አንዲት ሴት ስለ እርሱ ሰምታ መጣችና በእግሩ ላይ ተደፋች 26ሴቲቱም ግሪክ፥ ትውልድዋም ሲሮፊኒቃዊት ነበረች፤ ከልጅዋ ጋኔን ያወጣላት ዘንድ ለመነችው። 27ኢየሱስ ግን። ልጆቹ በፊት ይጠግቡ ዘንድ ተዪ የልጆቹን እንጀራ ይዞ ለቡችሎች መጣል አይገባምናአላት። 28እርስዋም መልሳ። አዎን፥ ጌታ ሆይ፥ ቡችሎች እንኳ ከማዕድ በታች ሆነው የልጆችን ፍርፋሪ ይበላሉ አለችው። 29እርሱም። ስለዚህ ቃልሽ ሂጂ ጋኔኑ ከልጅሽ ወጥቶአል አላት። 30ወደ ቤትዋም ሄዳ ጋኔኑ ወጥቶ ልጅዋም በአልጋ ላይ ተኝታ አገኘች። 31ደግሞም ከጢሮስ አገር ወጥቶ በሲዶና አልፎ አሥር ከተማ በሚባል አገር መካከል ወደ ገሊላ ባሕር መጣ። 32ደንቆሮና ኰልታፋም የሆነ ሰው ወደ እርሱ አመጡ፥ 33እጁንም ይጭንበት ዘንድ ለመኑት። ከሕዝቡም ለይቶ ለብቻው ወሰደው፥ ጣቶቹንም በጆሮቹ አገባ እንትፍም ብሎ መላሱን ዳሰሰ፤ 34ወደ ሰማይም አሻቅቦ አይቶ ቃተተና። ኤፍታህ አለው፥ እርሱም ተከፈት ማለት ነው። 35ወዲያውም ጆሮቹ ተከፈቱ የመላሱም እስራት ተፈታ አጥርቶም ተናገረ። 36ለማንም አትንገሩ ብሎ አዘዛቸው እነርሱ ግን ባዘዛቸውም መጠን ይልቅ እጅግ አወሩት። 37ያለ መጠንም ተገረሙና። ሁሉን ደኅና አድርጎአል፤ ደንቆሮችም እንዲሰሙ ዲዳዎችም እንዲናገሩ ያደርጋል አሉ።

Você sabia?

Pureza, tradição e o caminho além da Galileia

  • Fariseus e escribas vindos de Jerusalém questionaram Jesus porque alguns dos seus discípulos comiam com as mãos sem lavar. Marcos explica que, ao guardar a tradição dos anciãos, os fariseus e todos os judeus não comiam até se lavarem de modo cerimonial, e que também se lavavam ao voltar do mercado e lavavam copos, jarros, caldeirões e divãs. Uma cronologia data esse discurso sobre mandamentos e tradição do ano 29 d.C.Fontes: o próprio texto bíblico · Commandments and Tradition Discourse
  • Jesus respondeu citando Isaías, filho de Amoz, sobre um povo que honra a Deus com os lábios enquanto o coração está longe dele, e que ensina preceitos humanos como doutrina. À tradição dos anciãos ele contrapôs um mandamento que atribui a Moisés — honrar pai e mãe — e a prática do Corbã, que o texto explica como uma oferta dedicada a Deus e pela qual, segundo ele, a pessoa já não podia fazer nada pelo pai ou pela mãe.Fontes: o próprio texto bíblico · Isaiah
  • Na região de Tiro, uma mulher grega, de origem siro-fenícia, pediu a Jesus que expulsasse um espírito impuro de sua filha. Depois ele passou por Sidom, foi ao mar da Galileia e entrou na Decápolis: Sidom, no Mediterrâneo, ao norte de Tiro, era a cidade fenícia mais antiga e a cidade-mãe de Tiro, enquanto a Decápolis — nome que significa dez cidades — ficava a leste e a sudeste do lago e era habitada sobretudo por gregos. Ali lhe trouxeram um homem surdo que mal conseguia falar, e Jesus disse: “Efatá”, que a narrativa explica como “Abre-te”.Fontes: o próprio texto bíblico · Sidon · Tyre · Decapolis

Notas escritas com auxílio de IA a partir de fontes abertas (Theographic Bible Metadata, CC BY-SA 4.0; Easton’s Bible Dictionary, domínio público) e revisadas antes de publicar.

Lugares deste capítulo

  • Jerusalem · 31.777, 35.234 · versículo 1
  • Galilee · 32.760, 35.527 · versículo 24
  • Sidon · Hoje: Sandikli archaeological site in Sidon · 33.561, 35.372 · versículos 24, 31
  • Tyre · 33.271, 35.196 · versículos 24, 31
  • Phoenicia · 33.271, 35.196 · versículo 26
  • Decapolis · 32.717, 35.800 · versículo 31
  • Sea of Galilee · 32.819, 35.590 · versículo 31

Só aparecem lugares com identificação de alta confiança (90% ou mais segundo as fontes acadêmicas reunidas pelo OpenBible). Mapa da época: DARE (Digital Atlas of the Roman Empire), CC BY 4.0; mapa atual: © colaboradores do OpenStreetMap; lugares: OpenBible.info (CC BY 4.0).

Créditos e licença desta tradução
መጽሐፍ ቅዱስ
The New Testament in the Amharic language of Ethiopia
copyright © 1962, 2003 United Bible Societies
Language: አማርኛ (Amharic)
Amharic NT
Revised Amharic Bible in XML (2003).
Printed version by United Bible Societies (C)1962.
E-Text in transliterated ASCII format by Lapsley/Brooks Foundation 1994.
Unicode UTF-8 transformation and XML-tagging by Dirk Röckmann 2003 ( www.nt-text.net ).
With kind permission of the Bible Society of Ethiopia.
Every non-commercial work using this data in any form must fully include this copyright statement!
Every commercial use of parts or the complete data in any form needs written permission of the Bible Society of Ethiopia!
2014-09-09

Fonte: http://ebible.org/amh/ · eBible.org

Fale com a gente

Conte de onde você lê, como a Bíblia tem te ajudado ou o que podemos melhorar. Lemos todas as mensagens.