Marcos 3
መጽሐፍ ቅዱስ · Toque num versículo para ver as referências cruzadas.
1ደግሞም ወደ ምኵራብ ገባ፥ በዚያም እጁ የሰለለች ሰው ነበር፤ 2ሊከሱትም፥ በሰንበት ይፈውሰው እንደ ሆነ ይጠባበቁት ነበር። 3እጁ የሰለለችውንም ሰው። ተነሥተህ ወደ መካከል ና አለው። 4በሰንበት በጎ ማድረግ ተፈቅዶአልን? ወይስ ክፉ? ነፍስ ማዳን ወይስ መግደል? አላቸው፤ እነርሱም ዝም አሉ። 5ስለ ልባቸውም ድንዛዜ አዝኖ ዙሪያውን እየተመለከተ በቍጣ አያቸው፥ ሰውየውንም። እጅህን ዘርጋ አለው። 6ዘረጋትም፥ እጁም ዳነች። ፈሪሳውያንም ወጥተው ወዲያው እንዴት አድርገው እንዲያጠፉት ከሄሮድስ ወገን ጋር ተማከሩበት። 7ኢየሱስም ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደ ባህር ፈቀቅ አለ፤ ከገሊላ የመጡም ብዙ ሰዎች ተከተሉት፤ 8እንዴት ትልቅ ነገርም እንዳደረገው ሰምተው ብዙ ሰዎች ከይሁዳ ከኢየሩሳሌምም ከኤዶምያስም ከዮርዳኖስ ማዶም ከጢሮስና ከሲዶና ምድርም ወደ እርሱ መጡ። 9ሰዎቹም እንዳያጋፉት ታንኳን ያቆዩለት ዘንድ ደቀ መዛሙርቱን አዘዛቸው፤ 10ብዙ ሰዎችን አድኖ ነበርና፥ ስለዚህም ሥቃይ ያለባቸው ሁሉ እንዲዳስሱት ይወድቁበት ነበር። 11ርኵሳን መናፍስትም ባዩት ጊዜ በፊቱ ተደፍተው። አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ እያሉ ጮኹ። 12እንዳይገልጡትም በጣም አዘዛቸው። 13ወደ ተራራም ወጣ፥ ራሱም የወደዳቸውን ወደ እርሱ ጠራ፥ ወደ እርሱም ሄዱ። 14ከእርሱም ጋር እንዲኖሩና ለመስበክ እንዲልካቸው፥ 15ድውዮችንም ሊፈውሱ አጋንንትንም ሊያወጡ ሥልጣን ይሆንላቸው ዘንድ አሥራ ሁለት አደረገ፤ 16ስምዖንንም ጴጥሮስ ብሎ ሰየመው፤ 17የዘብዴዎስንም ልጅ ያዕቆብን የያዕቆብንም ወንድም ዮሐንስን ቦአኔርጌስ ብሎ ሰየማቸው፥ የነጎድጓድ ልጆች ማለት ነው፤ 18እንድርያስንም ፊልጶስንም በርተሎሜውስንም ማቴዎስንም ቶማስንም የእልፍዮስን ልጅ ያዕቆብንም ታዴዎስንም ቀነናዊውንም ስምዖንን፥ 19አሳልፎ የሰጠውንም የአስቆሮቱን ይሁዳን። 20ወደ ቤትም መጡ፤ እንጀራም መብላት ስንኳ እስኪሳናቸው ድረስ እንደ ገና ብዙ ሰዎች ተሰበሰቡ። 21ዘመዶቹም ሰምተው። አበደ ብለዋልና ሊይዙት ወጡ። 22ከኢየሩሳሌም የወረዱ ጻፎችም። ብዔል ዜቡል አለበት፤ ደግሞ። በአጋንንት አለቃ አጋንንትን ያወጣል ብለው ተናገሩ። 23እነርሱንም ወደ እርሱ ጠርቶ በምሳሌ አላቸው። ሰይጣን ሰይጣንን ሊያወጣው እንዴት ይችላል? 24መንግሥትም እርስ በርስዋ ከተለያየች ያች መንግሥት ልትቆም አትችልም፤ 25ቤትም እርስ በርሱ ከተለያየ ያ ቤት ሊቆም አይችልም። 26ሰይጣንም ራሱን ተቃውሞ ከተለያየ፥ መጨረሻ ይሆንበታል እንጂ ሊቆም አይችልም። 27ነገር ግን አስቀድሞ ኃይለኛውን ሳያስር ወደ ኃይለኛው ቤት ገብቶ ዕቃውን ሊበዘብዝ የሚችል የለም፥ ከዚያም ወዲያ ቤቱን ይበዘብዛል። 28እውነት እላችኋለሁ፥ ለሰው ልጆች ኃጢአት ሁሉ የሚሳደቡትም ስድብ ሁሉ ይሰረይላቸዋል፤ 29በመንፈስ ቅዱስ ላይ የሚሳደብ ሁሉ ግን የዘላለም ኃጢአት ዕዳ ይሆንበታል እንጂ ለዘላለም አይሰረይለትም። 30ርኵስ መንፈስ አለበት ይሉ ነበርና። 31እናቱና ወንድሞቹም መጡ በውጭም ቆመው ወደ እርሱ ልከው አስጠሩት። 32ብዙ ሰዎችም በዙሪያው ተቀምጠው ነበሩና። እነሆ፥ እናትህ ወንድሞችህም በውጭ ቆመው ይፈልጉሃል አሉት። 33መልሶም። እናቴ ማን ናት? ወንድሞቼስ እነ ማን ናቸው? አላቸው። 34በዙሪያው ተቀምጠው ወደ ነበሩትም ተመለከተና። እነሆ እናቴ ወንድሞቼም። 35የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ሁሉ፥ እርሱ ወንድሜ ነው እኅቴም እናቴም አለ።

Você sabia?
Multidões, os Doze e a acusação de Satanás
- Vários dos homens que Jesus designou como os doze tinham sido pescadores na Galileia. Simão, a quem ele deu o nome de Pedro, e seu irmão André eram de Betsaida; Tiago e João, filhos de Zebedeu, pescavam em sociedade com Pedro. Jesus chamou esses irmãos de Boanerges, “Filhos do Trovão”; o Dicionário Bíblico de Easton (1897) diz que provavelmente receberam esse nome por causa da ousadia e da energia deles.Fontes: Simon Peter · Andrew · James (Son of Zebedee) · o próprio texto bíblico
- Pessoas se apertavam vindas da Galileia, da Judeia, de Jerusalém, da Idumeia, de além do Jordão e da região de Tiro e Sidom, porque tinham ouvido o que Jesus fazia. Tiro e Sidom eram antigas cidades fenícias no Mediterrâneo; Sidom ficava cerca de vinte e cinco milhas ao norte de Tiro. Sob os romanos, a Judeia era a mais meridional das três divisões da Palestina, distinta da Galileia.Fontes: o próprio texto bíblico · Tyre · Sidon · Judea
- Escribas que tinham descido de Jerusalém diziam que Jesus estava possuído por Beelzebul e que expulsava demônios pelo príncipe dos demônios. Ele respondeu perguntando como Satanás pode expulsar Satanás. Satanás significa “adversário” ou “acusador”; no Novo Testamento o nome é usado de forma intercambiável com o diabo, e o Dicionário Bíblico de Easton (1897) também o chama de Beelzebub.Fontes: o próprio texto bíblico · Satan
Notas escritas com auxílio de IA a partir de fontes abertas (Theographic Bible Metadata, CC BY-SA 4.0; Easton’s Bible Dictionary, domínio público) e revisadas antes de publicar.
Lugares deste capítulo
- Galilee · 32.760, 35.527 · versículo 7
- Judea · Hoje: Judea 1 · 31.777, 35.234 · versículo 7
- Idumea · 31.525, 35.102 · versículo 8
- Jerusalem · 31.777, 35.234 · versículos 8, 22
- Jordan · Hoje: Jordan River · 31.761, 35.558 · versículo 8
- Sidon · Hoje: Sandikli archaeological site in Sidon · 33.561, 35.372 · versículo 8
- Tyre · 33.271, 35.196 · versículo 8
Só aparecem lugares com identificação de alta confiança (90% ou mais segundo as fontes acadêmicas reunidas pelo OpenBible). Mapa da época: DARE (Digital Atlas of the Roman Empire), CC BY 4.0; mapa atual: © colaboradores do OpenStreetMap; lugares: OpenBible.info (CC BY 4.0).
Créditos e licença desta tradução
መጽሐፍ ቅዱስ The New Testament in the Amharic language of Ethiopia copyright © 1962, 2003 United Bible Societies Language: አማርኛ (Amharic) Amharic NT Revised Amharic Bible in XML (2003). Printed version by United Bible Societies (C)1962. E-Text in transliterated ASCII format by Lapsley/Brooks Foundation 1994. Unicode UTF-8 transformation and XML-tagging by Dirk Röckmann 2003 ( www.nt-text.net ). With kind permission of the Bible Society of Ethiopia. Every non-commercial work using this data in any form must fully include this copyright statement! Every commercial use of parts or the complete data in any form needs written permission of the Bible Society of Ethiopia! 2014-09-09
Fonte: http://ebible.org/amh/ · eBible.org