Nations Bible

Mateus 22

መጽሐፍ ቅዱስ · Toque num versículo para ver as referências cruzadas.

1ኢየሱስም መለሰ ደግሞም በምሳሌ ነገራቸው እንዲህም አለ። 2መንግሥተ ሰማያት ለልጁ ሰርግ ያደረገ ንጉሥን ትመስላለች። 3የታደሙትንም ወደ ሰርጉ ይጠሩ ዘንድ ባሮቹን ላከ ሊመጡም አልወደዱም። 4ደግሞ ሌሎችን ባሮች ልኮ። የታደሙትን። እነሆ፥ ድግሴን አዘጋጀሁ፥ ኮርማዎቼና የሰቡት ከብቶቼ ታርደዋል፥ ሁሉም ተዘጋጅቶአል፤ ወደ ሰርጉ ኑ በሉአቸው አለ። 5እነርሱ ግን ቸል ብለው አንዱ ወደ እርሻው፥ ሌላውም ወደ ንግዱ ሄደ፤ 6የቀሩትም ባሮቹን ይዘው አንገላቱአቸው ገደሉአቸውም። 7ንጉሡም ተቈጣ፥ ጭፍሮቹንም ልኮ እነዚያን ገዳዮች አጠፋ፤ ከተማቸውንም አቃጠለ። 8በዚያን ጊዜ ባሮቹን። ሰርጉስ ተዘጋጅቶአል፥ ነገር ግን የታደሙት የማይገባቸው ሆኑ፤ 9እንግዲህ ወደ መንገድ መተላለፊያ ሄዳችሁ ያገኛችሁትን ሁሉ ወደ ሰርጉ ጥሩ አለ። 10እነዚያም ባሮች ወደ መንገድ ወጥተው ያገኙትን ሁሉ ክፉዎችንም በጎዎችንም ሰበሰቡ፤ የሰርጉንም ቤት ተቀማጮች ሞሉት። 11ንጉሡም የተቀመጡትን ለማየት በገባ ጊዜ በዚያ የሰርግ ልብስ ያለበሰ አንድ ሰው አየና። ወዳጄ ሆይ፥ 12የሰርግ ልብስ ሳትለብስ እንዴት ወደዚህ ገባህ? አለው እርሱም ዝም አለ። 13በዚያን ጊዜ ንጉሡ አገልጋዮቹን። እጁንና እግሩን አስራችሁ በውጭ ወዳለው ጨለማ አውጡት፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል አለ። 14የተጠሩ ብዙዎች፥ የተመረጡ ግን ጥቂቶች ናቸውና። 15ስለዚህ ፈሪሳውያን ሄዱና እንዴት አድርገው በነገር እንዲያጠምዱት ተማከሩ። 16ደቀ መዛሙርታቸውንም ከሄሮድስ ወገን ጋር ላኩበት፥ እነርሱም። መምህር ሆይ፥ እውነተኛ እንደ ሆንህ በእውነትም የእግዚአብሔርን መንገድ እንድታስተምር እናውቃለን፥ ለማንምም አታደላም፥ የሰውን ፊት አትመለከትምና፤ 17እንግዲህ ምን ይመስልሃል? ንገረን ለቄሣር ግብር መስጠት ተፈቅዶአልን ወይስ አልተፈቀደም? አሉት። 18ኢየሱስም ክፋታቸውን አውቆ። እናንተ ግብዞች፥ ስለ ምን ትፈትኑኛላችሁ? 19የግብሩን ብር አሳዩኝ አለ። እነርሱም ዲናር አመጡለት። 20እርሱም። ይህች መልክ ጽሕፈቲቱስ የማን ናት? አላቸው። 21የቄሣር ነው አሉት። በዚያን ጊዜ። እንኪያስ የቄሣርን ለቄሣር የእግዚአብሔርንም ለእግዚአብሔር አስረክቡ አላቸው። 22ይህንም ሰምተው ተደነቁ፥ ትተውትም ሄዱ። 23በዚያን ቀን። ትንሣኤ ሙታን የለም የሚሉ ሰዱቃውያን ወደ እርሱ ቀረቡ፥ 24እንዲህም ብለው ጠየቁት። መምህር ሆይ፥ ሙሴ አንድ ሰው ልጅ ሳይወልድ ሲሞት ወንድሙ ሚስቱን አግብቶ ለወንድሙ ዘር ይተካ አለ። 25ሰባት ወንድማማች በእኛ ዘንድ ነበሩ፤ ፊተኛውም ሚስት አግብቶ ሞተ፥ ዘርም ስለሌለው ሚስቱን ለወንድሙ ተወለት፤ 26እንዲሁ ደግሞ ሁለተኛው ሦስተኛውም፥ እስከ ሰባተኛው ድረስ። 27ከሁሉም በኋላ ሴቲቱ ሞተች። 28ሁሉ አግብተዋታልና በትንሣኤ ቀንስ፥ ከሰባቱ ለማናቸው ሚስት ትሆናለች? 29ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው። መጻሕፍትንና የእግዚአብሔርን ኃይል አታውቁምና ትስታላችሁ። 30በትንሣኤስ እንደ እግዚአብሔር መላእክት በሰማይ ይሆናሉ እንጂ አያገቡም አይጋቡምም። 31ሕዝቡም ይህን ሰምተው በትምህርቱ ተገረሙ። 34ፈሪሳውያንም ሰዱቃውያንን ዝም እንዳሰኛቸው በሰሙ ጊዜ አብረው ተሰበሰቡ። 35ከእነርሱም አንድ ሕግ አዋቂ ሊፈትነው። 36መምህር ሆይ፥ ከሕግ ማናቸይቱ ትእዛዝ ታላቅ ናት? ብሎ ጠየቀው። 37ኢየሱስም እንዲህ አለው። ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም አሳብህም ውደድ። 38ታላቂቱና ፊተኛይቱ ትእዛዝ ይህች ናት። 39ሁለተኛይቱም ይህችን ትመስላለች፥ እርስዋም። ባልንጀራህን እንደ ነፍስህ ውደድ የምትለው ናት። 40በእነዚህ በሁለቱ ትእዛዛት ሕጉም ሁሉ ነቢያትም ተሰቅለዋል። 41ዳዊትስ ጌታ ብሎ ከጠራው፥ እንዴት ልጁ ይሆናል? አላቸው። 46አንድም ቃል ስንኳ ይመልስለት ዘንድ የተቻለው የለም፥ ከዚያ ቀንም ጀምሮ ወደ ፊት ማንም ሊጠይቀው አልደፈረም።

Ilustração artística — interpretação, não registro histórico.

Você sabia?

Um banquete e um dia de perguntas

  • Os desafios deste capítulo acontecem todos no mesmo dia: fariseus e herodianos perguntam se é lícito pagar impostos a César, saduceus que dizem não haver ressurreição contam o caso de sete irmãos e uma viúva, e um especialista na Lei pergunta qual é o maior mandamento. Uma lista do episódio o chama de Debates no Templo e lhe atribui a duração de um dia; a narrativa acrescenta que, a partir daquele dia, ninguém mais ousou interrogar Jesus.Fontes: o próprio texto bíblico · Debates in the Temple
  • Ao responder aos saduceus, Jesus cita as palavras “Eu sou o Deus de Abraão, o Deus de Isaque e o Deus de Jacó” e diz que Deus não é Deus dos mortos, mas dos vivos. Um dicionário bíblico chama Abraão, filho de Terá, de pai de uma multidão; descreve Isaque como o único filho de Abraão com Sara e o mais longevo dos três patriarcas; e identifica Jacó, também chamado Israel, como o mais novo dos filhos gêmeos de Isaque e Rebeca.Fontes: o próprio texto bíblico · Abraham · Isaac · Jacob (Israel)
  • Perguntados de quem o Cristo é filho, os fariseus respondem que é de Davi. Um verbete de dicionário explica o nome Davi como Amado e o identifica como o oitavo e mais novo filho de Jessé, cidadão de Belém. Jesus então pergunta como Davi, falando no Espírito, pode chamar o Cristo de Senhor, e ninguém consegue responder.Fontes: o próprio texto bíblico · David

Notas escritas com auxílio de IA a partir de fontes abertas (Theographic Bible Metadata, CC BY-SA 4.0; Easton’s Bible Dictionary, domínio público) e revisadas antes de publicar.

Créditos e licença desta tradução
መጽሐፍ ቅዱስ
The New Testament in the Amharic language of Ethiopia
copyright © 1962, 2003 United Bible Societies
Language: አማርኛ (Amharic)
Amharic NT
Revised Amharic Bible in XML (2003).
Printed version by United Bible Societies (C)1962.
E-Text in transliterated ASCII format by Lapsley/Brooks Foundation 1994.
Unicode UTF-8 transformation and XML-tagging by Dirk Röckmann 2003 ( www.nt-text.net ).
With kind permission of the Bible Society of Ethiopia.
Every non-commercial work using this data in any form must fully include this copyright statement!
Every commercial use of parts or the complete data in any form needs written permission of the Bible Society of Ethiopia!
2014-09-09

Fonte: http://ebible.org/amh/ · eBible.org

Fale com a gente

Conte de onde você lê, como a Bíblia tem te ajudado ou o que podemos melhorar. Lemos todas as mensagens.