Mateus 19
መጽሐፍ ቅዱስ · Toque num versículo para ver as referências cruzadas.
1ኢየሱስም ይህን ነገር ከፈጸመ በኋላ፥ ከገሊላ ሄዶ ወደ ይሁዳ አውራጃ ወደ ዮርዳኖስ ማዶ መጣ። 2ብዙ ሕዝብም ተከተሉት፥ በዚያም ፈወሳቸው። 3ፈሪሳውያንም ወደ እርሱ ቀረቡና ሲፈትኑት። ሰው በሆነው ምክንያት ሁሉ ሚስቱን ሊፈታ ተፈቅዶለታልን? አሉት። 4እርሱ ግን መልሶ እንዲህ አለ። ፈጣሪ በመጀመሪያ ወንድና ሴት አደረጋቸው፥ 5አለም። ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል፥ ከሚስቱም ጋር ይተባበራል፥ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ የሚለውን ቃል አላነበባችሁምን? 6ስለዚህ አንድ ሥጋ ናቸው እንጂ ወደ ፊት ሁለት አይደሉም። እግዚአብሔር ያጣመረውን እንግዲህ ሰው አይለየው። 7እነርሱም። እንኪያስ ሙሴ የፍችዋን ጽሕፈት ሰጥተው እንዲፈቱአት ስለ ምን አዘዘ? አሉት። 8እርሱም። ሙሴስ ስለ ልባችሁ ጥንካሬ ሚስቶቻችሁን ትፈቱ ዘንድ ፈቀደላችሁ፤ ከጥንት ግን እንዲህ አልነበረም። 9እኔ ግን እላችኋለሁ፥ ያለ ዝሙት ምክንያት ሚስቱን ፈትቶ ሌላዪቱን የሚያገባ ሁሉ ያመነዝራል፥ የተፈታችውንም የሚያገባ ያመነዝራል አላቸው። 10ደቀ መዛሙርቱም። የባልና የሚስት ሥርዓት እንዲህ ከሆነ መጋባት አይጠቅምም አሉት። 11እርሱ ግን። ይህ ነገር ለተሰጣቸው ነው እንጂ ለሁሉ አይደለም፤ 12በእናት ማኅፀን ጃንደረቦች ሆነው የተወለዱ አሉ፥ ሰውም የሰለባቸው ጃንደረቦች አሉ፥ ስለ መንግሥተ ሰማያትም ራሳቸውን የሰለቡ ጃንደረቦች አሉ። ሊቀበለው የሚችል ይቀበለው አላቸው። 13በዚያን ጊዜ እጁን እንዲጭንባቸውና እንዲጸልይ ሕፃናትን ወደ እርሱ አመጡ፤ ደቀ መዛሙርቱም ገሠጹአቸው። 14ነገር ግን ኢየሱስ። ሕፃናትን ተዉአቸው፥ ወደ እኔም ይመጡ ዘንድ አትከልክሉአቸው፤ መንግሥተ ሰማያት እንደነዚህ ላሉ ናትና አለ፤ 15እጁንም ጫነባቸውና ከዚያ ሄደ። 16እነሆም፥ አንድ ሰው ቀርቦ። መምህር ሆይ፥ የዘላለምን ሕይወት እንዳገኝ ምን መልካም ነገር ላድርግ? አለው። 17እርሱም። ስለ መልካም ነገር ለምን ትጠይቀኛለህ? መልካም የሆነ አንድ ነው፤ ወደ ሕይወት መግባት ብትወድ ግን ትእዛዛትን ጠብቅ አለው። 18እርሱም። የትኞችን? አለው። ኢየሱስም። አትግደል፥ አታመንዝር፥ አትስረቅ፥ በሐሰት አትመስክር፥ 19አባትህንና እናትህን አክብር፥ ባልንጀራህንም እንደ ራስህ ውደድ አለው። 20ጐበዙም። ይህንማ ሁሉ ከሕፃንነቴ ጀምሬ ጠብቄአለሁ፥ ደግሞስ የሚጐድለኝ ምንድር ነው? አለው። 21ኢየሱስም። ፍጹም ልትሆን ብትወድ፥ ሂድና ያለህን ሸጠህ ለድሆች ስጥ፥ መዝገብም በሰማያት ታገኛለህ፥ መጥተህም ተከተለኝ አለው። 22ጐበዙም ይህን ቃል በሰማ ጊዜ ብዙ ንብረት ነበረውና እያዘነ ሄደ። 23ኢየሱስም ለደቀ መዛሙርቱ። እውነት እላችኋለሁ፥ ለባለጠጋ ወደ መንግሥተ ሰማያት መግባት ጭንቅ ነው። 24ዳግመኛም እላችኋለሁ፥ ባለጠጋ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢገባ ይቀላል አለ። 25ደቀ መዛሙርቱም ሰምተው እጅግ ተገረሙና። እንኪያስ ማን ሊድን ይችላል? አሉ። 26ኢየሱስም እነርሱን ተመልክቶ። ይህ በሰው ዘንድ አይቻልም በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ሁሉ ይቻላል አላቸው። 27በዚያን ጊዜ ጴጥሮስ መልሶ። እነሆ፥ እኛ ሁሉን ትተን ተከተልንህ፤ እንኪያስ ምን እናገኝ ይሆን? አለው። 28ኢየሱስም እንዲህ አላቸው። እውነት እላችኋለሁ፥ እናንተስ የተከተላችሁኝ፥ በዳግመኛ ልደት የሰው ልጅ በክብሩ ዙፋን በሚቀመጥበት ጊዜ፥ እናንተ ደግሞ በአሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ ስትፈርዱ በአሥራ ሁለት ዙፋን ትቀመጣላችሁ። 29ስለ ስሜም ቤቶችን ወይም ወንድሞችን ወይም እኅቶችን ወይም አባትን ወይም እናትን ወይም ሚስትን ወይም ልጆችን ወይም እርሻን የተወ ሁሉ መቶ እጥፍ ይቀበላል የዘላለምንም ሕይወት ይወርሳል። 30ነገር ግን ብዙዎቹ ፊተኞች ኋለኞች፥ ኋለኞችም ፊተኞች ይሆናሉ።

Você sabia?
Casamento, crianças e o custo de seguir
- Depois de concluir essas palavras, Jesus deixou a Galileia e foi para a região da Judeia além do Jordão, onde grandes multidões o seguiram e ele as curou. Os judeus chamavam a Galileia de Galil; ela também era conhecida como Galileia dos gentios, e a Galileia Superior se distinguia da Inferior. Sob os romanos, no tempo de Cristo, a Judeia era a mais ao sul das três divisões da Palestina, distinta da Galileia e da Samaria, e um relato datado chama esse ensino de ensino na Pereia, com início no ano 30 d.C.Fontes: o próprio texto bíblico · Galilee · Judea · Jesus Teaches in Perea
- Alguns fariseus vieram para pôr Jesus à prova, perguntando se era lícito a um homem divorciar-se da mulher por qualquer motivo, e apelaram à ordem de Moisés de que o homem desse à mulher uma certidão de divórcio e a despedisse. Jesus respondeu que Moisés permitiu o divórcio por causa da dureza de coração deles, embora não fosse assim desde o princípio.Fontes: o próprio texto bíblico
- Quando Pedro disse que ele e os outros tinham deixado tudo para seguir Jesus, falava como quem fora preparado para ser pescador. Chamado originalmente Simão, era filho de Jona, e sua cidade natal era Betsaida, na costa ocidental do mar da Galileia, onde fora criado nesse ofício.Fontes: o próprio texto bíblico · Simon Peter
Notas escritas com auxílio de IA a partir de fontes abertas (Theographic Bible Metadata, CC BY-SA 4.0; Easton’s Bible Dictionary, domínio público) e revisadas antes de publicar.
Lugares deste capítulo
- Galilee · 32.760, 35.527 · versículo 1
- Jordan · Hoje: Jordan River · 31.761, 35.558 · versículo 1
- Judea · Hoje: Judea 1 · 31.777, 35.234 · versículo 1
Só aparecem lugares com identificação de alta confiança (90% ou mais segundo as fontes acadêmicas reunidas pelo OpenBible). Mapa da época: DARE (Digital Atlas of the Roman Empire), CC BY 4.0; mapa atual: © colaboradores do OpenStreetMap; lugares: OpenBible.info (CC BY 4.0).
Créditos e licença desta tradução
መጽሐፍ ቅዱስ The New Testament in the Amharic language of Ethiopia copyright © 1962, 2003 United Bible Societies Language: አማርኛ (Amharic) Amharic NT Revised Amharic Bible in XML (2003). Printed version by United Bible Societies (C)1962. E-Text in transliterated ASCII format by Lapsley/Brooks Foundation 1994. Unicode UTF-8 transformation and XML-tagging by Dirk Röckmann 2003 ( www.nt-text.net ). With kind permission of the Bible Society of Ethiopia. Every non-commercial work using this data in any form must fully include this copyright statement! Every commercial use of parts or the complete data in any form needs written permission of the Bible Society of Ethiopia! 2014-09-09
Fonte: http://ebible.org/amh/ · eBible.org