Atos 11
መጽሐፍ ቅዱስ · Toque num versículo para ver as referências cruzadas.
1ሐዋርያትና በይሁዳም የነበሩት ወንድሞች አሕዛብ ደግሞ የእግዚአብሔርን ቃል እንደ ተቀበሉ ሰሙ። 2ጴጥሮስም ወደ ኢየሩሳሌም በወጣ ጊዜ ከተገረዙት ወገን የሆኑት ሰዎች ከእርሱ ጋር ተከራክረው። 3ወዳልተገረዙ ሰዎች ገብተህ ከእነርሱ ጋር በላህ አሉት። 4ጴጥሮስ ግን ከመጀመሪያው ጀምሮ በተራ ገለጠላቸው እንዲህም አለ። 5እኔ በኢዮጴ ከተማ ስጸልይ ሳለሁ ተመስጬ ራእይን አየሁ፤ ታላቅ ሸማ የመሰለ ዕቃ በአራት ማዕዘን ተይዞ ከሰማይ ወረደና ወደ እኔ መጣ፤ 6ይህንም ትኵር ብዬ ስመለከት አራት እግር ያላቸውን የምድር እንስሶች አራዊትንም ተንቀሳቃሾችንም የሰማይ ወፎችንም አየሁ። 7ጴጥሮስ ሆይ፥ ተነሣና አርደህ ብላ የሚለኝንም ድምፅ ሰማሁ። 8እኔም። ጌታ ሆይ፥ አይሆንም፤ ርኵስ ወይም የሚያስጸይፍ ከቶ ወደ አፌ ገብቶ አያውቅምና አልሁ። 9ሁለተኛም። እግዚአብሔር ያነጻውን አንተ አታርክሰው የሚል ድምፅ ከሰማይ መለሰልኝ። 10ይህም ሦስት ጊዜ ሆነ እንደ ገናም ሁሉ ወደ ሰማይ ተሳበ። 11እነሆም፥ ያን ጊዜ ሦስት ሰዎች ከቂሣርያ ወደ እኔ ተልከው ወዳለሁበት ቤት ቀረቡ። 12መንፈስም ሳልጠራጠር ከእነርሱ ጋር እሄድ ዘንድ ነገረኝ። እነዚህም ስድስቱ ወንድሞች ደግሞ ከእኔ ጋር መጡ ወደዚያ ሰውም ቤት ገባን። 13እርሱም መልአክ በቤቱ ቆሞ እንዳየና። ወደ ኢዮጴ ሰዎች ልከህ ጴጥሮስ የተባለውን ስምዖንን አስመጣ፤ 14እርሱም አንተና የቤትህ ሰዎች ሁሉ የምትድኑበትን ነገር ይነግርሃል እንዳለው ነገረን። 15ለመናገርም በጀመርሁ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ለእኛ ደግሞ በመጀመሪያ እንደ ወረደ ለእነርሱ ወረደላቸው። 16ዮሐንስ በውኃ አጠመቀ እናንተ ግን በመንፈስ ቅዱስ ትጠመቃላችሁ ያለውም የጌታ ቃል ትዝ አለኝ። 17እንግዲህ እግዚአብሔር በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ላመነው ለእኛ ደግሞ እንደ ሰጠን ያን ስጦታ ለእነርሱ ከሰጠ፥ እግዚአብሔርን ለመከልከል እችል ዘንድ እኔ ማን ነበርሁ? 18ይህን በሰሙ ጊዜም ዝም አሉና። እንኪያስ እግዚአብሔር ለአሕዛብ ደግሞ ለሕይወት የሚሆን ንስሐን ሰጣቸው እያሉ እግዚአብሔርን አከበሩ። 19በእስጢፋኖስም ላይ በተደረገው መከራ የተበተኑት እስከ ፊንቄ እስከ ቆጵሮስም እስከ አንጾኪያም ድረስ ዞሩ፥ ቃሉንም ለአይሁድ ብቻ እንጂ ለአንድ ስንኳ አይናገሩም ነበር። 20ከእነርሱ ግን የቆጵሮስና የቀሬና ሰዎች የነበሩት አንዳንዶቹ ወደ አንጾኪያ መጥተው የጌታን የኢየሱስን ወንጌል እየሰበኩ ለግሪክ ሰዎች ተናገሩ። 21የጌታም እጅ ከእነርሱ ጋር ነበረ፤ ቍጥራቸውም እጅግ የሚሆን ሰዎች አምነው ወደ ጌታ ዘወር አሉ። 22ወሬውም በኢየሩሳሌም ባለችው ቤተ ክርስቲያን ስለ እነርሱ ተሰማ፥ በርናባስንም ወደ አንጾኪያ ላኩት፤ 23እርሱም መጥቶ የእግዚአብሔርን ጸጋ ባየ ጊዜ ደስ አለው፥ ሁሉንም በልባቸው ፈቃድ በጌታ ጸንተው ይኖሩ ዘንድ መከራቸው፤ 24ደግ ሰውና መንፈስ ቅዱስ እምነትም የሞላበት ነበረና። ብዙ ሕዝብም ወደ ጌታ ተጨመሩ። 25በርናባስም ሳውልን ሊፈልግ ወደ ጠርሴስ መጣ፤ 26ባገኘውም ጊዜ ወደ አንጾኪያ አመጣው። በቤተ ክርስቲያንም አንድ ዓመት ሙሉ ተሰበሰቡ፥ ብዙ ሕዝብንም አስተማሩ፤ ደቀ መዛሙርትም መጀመሪያ በአንጾኪያ ክርስቲያን ተባሉ። 27በዚያም ወራት ነቢያት ከኢየሩሳሌም ወደ አንጾኪያ ወረዱ፤ 28ከእነርሱም አጋቦስ የሚሉት አንድ ሰው ተነሥቶ በዓለም ሁሉ ታላቅ ራብ ሊሆን እንዳለው በመንፈስ አመለከተ፤ ይህም በቀላውዴዎስ ቄሣር ዘመን ሆነ። 29ደቀ መዛሙርትም እያንዳንዳቸው እንደ ችሎታቸው መጠን አዋጥተው በይሁዳ ለሚኖሩት ወንድሞች እርዳታን ይልኩ ዘንድ ወሰኑ፤ 30እንዲህም ደግሞ አደረጉ፥ በበርናባስና በሳውልም እጅ ወደ ሽማግሌዎቹ ሰደዱት።

Você sabia?
Gentios acolhidos e o nome cristão
- Quando Pedro subiu a Jerusalém, os crentes circuncidados o contestaram por ter visitado homens incircuncisos e comido com eles. Ele contou que, enquanto orava em Jope, o principal porto da Judeia, a trinta milhas a noroeste de Jerusalém, teve uma visão, e que o Espírito Santo caiu depois sobre uma família em Cesareia, capital romana da Judeia e sua grande cidade gentia. Uma cronologia desses acontecimentos situa essa defesa em 38 d.C.Fontes: o próprio texto bíblico · Joppa · Caesarea · Peter defends Gentile salvation
- Os que foram dispersos pela perseguição iniciada com Estêvão, o primeiro mártir cristão, chegaram até a Fenícia, Chipre e Antioquia, falando a princípio apenas aos judeus. Antioquia, às margens do Orontes, a cerca de dezesseis milhas do Mediterrâneo e umas trezentas milhas ao norte de Jerusalém, era a metrópole da Síria e ocupava o terceiro lugar em importância entre as cidades do império romano, depois de Roma e Alexandria; era chamada a primeira cidade do Oriente. Ali os discípulos foram chamados cristãos pela primeira vez, o que uma cronologia situa em 40 d.C.Fontes: o próprio texto bíblico · Stephen · Antioch (Syria) · Disciples first called Christians
- A igreja de Jerusalém enviou Barnabé, levita de Chipre a quem o relato chama homem bom, cheio do Espírito Santo e de fé; ele encontrou Saulo em Tarso e o levou a Antioquia, onde ensinaram a igreja durante um ano inteiro. O profeta Ágabo predisse então, pelo Espírito, que uma grande fome se espalharia por todo o mundo, o que a narrativa diz ter ocorrido sob Cláudio. O Easton's Bible Dictionary (1897) identifica Cláudio como o quarto imperador romano, que sucedeu Calígula em 41 d.C. e morreu em 54 d.C., e os discípulos enviaram socorro aos irmãos da Judeia por meio de Barnabé e Saulo.Fontes: o próprio texto bíblico · Barnabas · Agabus · Claudius (4th Roman Emperor)
Notas escritas com auxílio de IA a partir de fontes abertas (Theographic Bible Metadata, CC BY-SA 4.0; Easton’s Bible Dictionary, domínio público) e revisadas antes de publicar.
Lugares deste capítulo
- Judea · Hoje: Judea 1 · 31.777, 35.234 · versículos 1, 29
- Jerusalem · 31.777, 35.234 · versículos 2, 22, 27, 30
- Joppa · Hoje: Jaffa · 32.054, 34.753 · versículos 5, 13
- Caesarea · Hoje: Caesarea Maritima · 32.500, 34.892 · versículo 11
- Antioch · Hoje: Antioch on the Orontes · 36.227, 36.172 · versículos 19, 20, 22, 26, 27, 29
- Cyprus · 35.000, 33.000 · versículos 19, 20
- Phoenicia · 33.271, 35.196 · versículo 19
- Cyrene · 32.821, 21.851 · versículo 20
- Tarsus · 36.913, 34.892 · versículo 25
Só aparecem lugares com identificação de alta confiança (90% ou mais segundo as fontes acadêmicas reunidas pelo OpenBible). Mapa da época: DARE (Digital Atlas of the Roman Empire), CC BY 4.0; mapa atual: © colaboradores do OpenStreetMap; lugares: OpenBible.info (CC BY 4.0).
Créditos e licença desta tradução
መጽሐፍ ቅዱስ The New Testament in the Amharic language of Ethiopia copyright © 1962, 2003 United Bible Societies Language: አማርኛ (Amharic) Amharic NT Revised Amharic Bible in XML (2003). Printed version by United Bible Societies (C)1962. E-Text in transliterated ASCII format by Lapsley/Brooks Foundation 1994. Unicode UTF-8 transformation and XML-tagging by Dirk Röckmann 2003 ( www.nt-text.net ). With kind permission of the Bible Society of Ethiopia. Every non-commercial work using this data in any form must fully include this copyright statement! Every commercial use of parts or the complete data in any form needs written permission of the Bible Society of Ethiopia! 2014-09-09
Fonte: http://ebible.org/amh/ · eBible.org