Nations Bible

1 Pedro 2

መጽሐፍ ቅዱስ · Toque num versículo para ver as referências cruzadas.

1እንግዲህ ክፋትን ሁሉ ተንኰልንም ሁሉ ግብዝነትንም ቅንዓትንም ሐሜትንም ሁሉ አስወግዳችሁ፥ 2በሰውም ወደ ተጣለ በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ወደ ተመረጠና ክቡር ወደ ሆነው ወደ ሕያው ድንጋይ ወደ እርሱ እየቀረባችሁ፥ 5እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ታቀርቡ ዘንድ ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ። 6በመጽሐፍ። እነሆ፥ የተመረጠና የከበረን የማዕዘን ራስ ድንጋይ በጽዮን አኖራለሁ በእርሱም የሚያምን አያፍርም ተብሎ ተጽፎአልና። 7እንግዲህ ክብሩ ለእናንተ ለምታምኑት ነው፤ ለማያምኑ ግን አናጢዎች የጣሉት ድንጋይ እርሱ የማዕዘን ራስ የዕንቅፋትም ድንጋይ የማሰናከያም ዓለት ሆነ፤ 8የማያምኑ ስለ ሆኑ በቃሉ ይሰናከሉበታልና፤ ለዚህ ደግሞ የተመደቡ ናቸው። 9እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤ 10እናንተ ቀድሞ ወገን አልነበራችሁም አሁን ግን የእግዚአብሔር ወገን ናችሁ፤ እናንተ ምሕረት ያገኛችሁ አልነበራችሁም አሁን ግን ምሕረትን አግኝታችኋል። 11ወዳጆች ሆይ፥ ነፍስን ከሚዋጋ ሥጋዊ ምኞት ትርቁ ዘንድ እንግዶችና መጻተኞች እንደ መሆናችሁ እለምናችኋለሁ፤ 12ስለሚመለከቱት ስለ መልካም ሥራችሁ፥ ክፉ እንደምታደርጉ በዚያ እናንተን በሚያሙበት ነገር፥ በሚጎበኝበት ቀን እግዚአብሔርን ያከብሩት ዘንድ በአሕዛብ መካከል ኑሮአችሁ መልካም ይሁን። 13ስለ ጌታ ብላችሁ ለሰው ሥርዓት ሁሉ ተገዙ፤ ለንጉሥም ቢሆን፥ ከሁሉ በላይ ነውና፤ 14ለመኳንንትም ቢሆን፥ ክፉ የሚያደርጉትን ለመቅጣት በጎም የሚያደርጉትን ለማመስገን ከእርሱ ተልከዋልና ተገዙ። 15በጎ እያደረጋችሁ፥ የማያውቁትን ሞኞች ዝም ታሰኙ ዘንድ እንዲህ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነውና፤ 16አርነት ወጥታችሁ እንደ እግዚአብሔር ባሪያዎች ሁኑ እንጂ ያ አርነት ለክፋት መሸፈኛ እንዲሆን አታድርጉ። 17ሁሉን አክብሩ፥ ወንድሞችን ውደዱ፥ እግዚአብሔርን ፍሩ፥ ንጉሥን አክብሩ። 18ሎሌዎች ሆይ፥ ለበጎዎችና ለገሮች ጌቶቻችሁ ብቻ ሳይሆን ለጠማሞች ደግሞ በፍርሃት ሁሉ ተገዙ። 19በግፍ መከራን የሚቀበል ሰው እግዚአብሔርን እያሰበ ኃዘንን ቢታገሥ ምስጋና ይገባዋልና። 20ኃጢአት አድርጋችሁ ስትጎሰሙ ብትታገሡ፥ ምን ክብር አለበት? ነገር ግን መልካም አድርጋችሁ መከራን ስትቀበሉ ብትታገሡ፥ ይህ ነገር በእግዚአብሔር ዘንድ ምስጋና ይገባዋል። 21የተጠራችሁለት ለዚህ ነውና፤ ክርስቶስ ደግሞ ፍለጋውን እንድትከተሉ ምሳሌ ትቶላችሁ ስለ እናንተ መከራን ተቀብሎአልና። 22እርሱም ኃጢአት አላደረገም፥ ተንኰልም በአፉ አልተገኘበትም፤ 23ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም መከራንም ሲቀበል አልዛተም፥ ነገር ግን በጽድቅ ለሚፈርደው ራሱን አሳልፎ ሰጠ፤ 24ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ፤*ፍ1* 25በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ። እንደ በጎች ትቅበዘበዙ ነበርና፥ አሁን ግን ወደ ነፍሳችሁ እረኛና ጠባቂ ተመልሳችኋል።

Ilustração artística — interpretação, não registro histórico.

Você sabia?

Pedras vivas e um povo escolhido

  • Este capítulo cita a Escritura sobre uma pedra angular escolhida e preciosa colocada em Sião: quem nela crê jamais será envergonhado. Sião era a colina do sudeste de Jerusalém, uma das elevações sobre as quais a cidade foi construída, cercada por vales profundos de todos os lados, exceto o norte.Fontes: o próprio texto bíblico · Zion
  • Davi tomou Sião dos jebuseus, construiu ali uma cidadela e um palácio, e a colina passou a ser conhecida como a cidade de Davi. A carta usa esse nome de lugar ao citar a Escritura sobre uma pedra angular colocada em Sião e descreve os leitores como pedras vivas, edificadas como casa espiritual e sacerdócio santo.Fontes: Zion · o próprio texto bíblico
  • O capítulo exorta à submissão, por causa do Senhor, a toda instituição humana: ao rei, como autoridade suprema, e aos governadores enviados para punir os que fazem o mal e louvar os que fazem o bem. Diz aos servos que respeitem até os senhores que agem sem razão, e apresenta o sofrimento de Cristo — sem pecado, sem engano, sem ameaças e sem retaliação — como modelo para suportar a dor injusta.Fontes: o próprio texto bíblico

Notas escritas com auxílio de IA a partir de fontes abertas (Theographic Bible Metadata, CC BY-SA 4.0; Easton’s Bible Dictionary, domínio público) e revisadas antes de publicar.

Lugares deste capítulo

  • Zion · Hoje: Jerusalem · 31.777, 35.234 · versículo 6

Só aparecem lugares com identificação de alta confiança (90% ou mais segundo as fontes acadêmicas reunidas pelo OpenBible). Mapa da época: DARE (Digital Atlas of the Roman Empire), CC BY 4.0; mapa atual: © colaboradores do OpenStreetMap; lugares: OpenBible.info (CC BY 4.0).

Créditos e licença desta tradução
መጽሐፍ ቅዱስ
The New Testament in the Amharic language of Ethiopia
copyright © 1962, 2003 United Bible Societies
Language: አማርኛ (Amharic)
Amharic NT
Revised Amharic Bible in XML (2003).
Printed version by United Bible Societies (C)1962.
E-Text in transliterated ASCII format by Lapsley/Brooks Foundation 1994.
Unicode UTF-8 transformation and XML-tagging by Dirk Röckmann 2003 ( www.nt-text.net ).
With kind permission of the Bible Society of Ethiopia.
Every non-commercial work using this data in any form must fully include this copyright statement!
Every commercial use of parts or the complete data in any form needs written permission of the Bible Society of Ethiopia!
2014-09-09

Fonte: http://ebible.org/amh/ · eBible.org

Fale com a gente

Conte de onde você lê, como a Bíblia tem te ajudado ou o que podemos melhorar. Lemos todas as mensagens.