1 João 5
መጽሐፍ ቅዱስ · Toque num versículo para ver as referências cruzadas.
1ክርስቶስ ነው ብሎ በኢየሱስ የሚያምን ሁሉ ከእግዚአብሔር ተወልዶአል፥ ወላጁንም የሚወድ ሁሉ ከእርሱ የተወለደውን ደግሞ ይወዳል። 2እግዚአብሔርን ስንወድ ትእዛዛቱንም ስናደርግ የእግዚአብሔርን ልጆች እንድንወድ በዚህ እናውቃለን። 3ትእዛዛቱን ልንጠብቅ የእግዚአብሔር ፍቅር ይህ ነውና፤ ትእዛዛቱም ከባዶች አይደሉም። 4ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ዓለምን ያሸንፋልና፤ ዓለምንም የሚያሸንፈው እምነታችን ነው። 5ኢየሱስም የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ ከሚያምን በቀር ዓለምን የሚያሸንፍ ማን ነው? 6በውኃና በደም የመጣ ይህ ነው እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ፤ በውኃውና በደሙ እንጂ በውኃው ብቻ አይደለም። 7መንፈስም እውነት ነውና የሚመሰክረው መንፈስ ነው። 8የሚመሰክሩት መንፈሱና ውኃው ደሙም ሦስት ናቸውና፤ ሦስቱም በአንድ ይስማማሉ። 9የሰውን ምስክር ብንቀበል የእግዚአብሔር ምስክር ከእርሱ ይልቅ ይበልጣል፤ ስለ ልጁ የመሰከረው የእግዚአብሔር ምስክር ይህ ነውና። 10በእግዚአብሔር ልጅ የሚያምን በነፍሱ ምስክር አለው፤ በእግዚአብሔር የማያምን እግዚአብሔር ስለ ልጁ የመሰከረውን ምስክር ስላላመነ ሐሰተኛ አድርጎታል። 11እግዚአብሔርም የዘላለምን ሕይወት እንደ ሰጠን ይህም ሕይወት በልጁ እንዳለ ምስክሩ ይህ ነው። 12ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም። 13የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ታውቁ ዘንድ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ለምታምኑ ይህን ጽፌላችኋለሁ። 14በእርሱ ዘንድ ያለን ድፍረት ይህ ነው፤ እንደ ፈቃዱ አንዳች ብንለምን ይሰማናል። 15የምንለምነውንም ሁሉ እንዲሰማልን ብናውቅ ከእርሱ የለመነውን ልመና እንደ ተቀበልን እናውቃለን። 16ማንም ወንድሙን ሞት የማይገባውን ኃጢአት ሲያደርግ ቢያየው ይለምን፥ ሞትም የማይገባውን ኃጢአት ላደረጉት ሕይወት ይሰጥለታል። ሞት የሚገባው ኃጢአት አለ፤ ስለዚያ እንዲጠይቅ አልልም። 17ዓመፃ ሁሉ ኃጢአት ነው፥ ሞትም የማይገባው ኃጢአት አለ። 18ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ኃጢአትን እንዳያደርግ፥ ነገር ግን ከእግዚአብሔር የተወለደው ራሱን እንዲጠብቅ ክፉውም እንዳይነካው እናውቃለን። 19ከእግዚአብሔር እንደ ሆንን ዓለምም በሞላው በክፉው እንደ ተያዘ እናውቃለን። 20የእግዚአብሔርም ልጅ እንደ መጣ፥ እውነተኛም የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቡናን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እውነተኛም በሆነው በእርሱ አለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው። 21ልጆች ሆይ፥ ከጣዖታት ራሳችሁን ጠብቁ።

Você sabia?
Fé, testemunho e vida
- Este capítulo diz que todo aquele que crê que Jesus é o Cristo é nascido de Deus, e que amar o Pai também significa amar os que nasceram dele. Descreve o amor a Deus como guardar os seus mandamentos, que não são pesados, porque todo aquele que nasceu de Deus vence o mundo, e chama essa vitória de fé em Jesus como Filho de Deus.Fontes: o próprio texto bíblico
- Jesus Cristo é apresentado como quem veio pela água e pelo sangue, não somente pela água, e o Espírito é quem testifica isso, porque o Espírito é a verdade; o capítulo não explica aqui o que são a água e o sangue. Apresenta o Espírito, a água e o sangue como três que testificam em acordo, e chama o testemunho de Deus acerca do seu Filho de maior que o testemunho humano: Deus nos deu a vida eterna, e essa vida está no seu Filho. O autor diz que escreveu essas coisas para que os que creem no nome do Filho de Deus saibam que têm a vida eterna.Fontes: o próprio texto bíblico
- Os leitores são orientados a pedir a Deus por um irmão que comete um pecado que não leva à morte, enquanto o autor diz que não está dizendo que peçam a respeito de um pecado que leva à morte. Ele não nomeia nenhum dos dois pecados, embora diga que toda injustiça é pecado e que há pecado que não leva à morte. O capítulo termina dizendo aos filhinhos que se guardem dos ídolos.Fontes: o próprio texto bíblico
Notas escritas com auxílio de IA a partir de fontes abertas (Theographic Bible Metadata, CC BY-SA 4.0; Easton’s Bible Dictionary, domínio público) e revisadas antes de publicar.
Créditos e licença desta tradução
መጽሐፍ ቅዱስ The New Testament in the Amharic language of Ethiopia copyright © 1962, 2003 United Bible Societies Language: አማርኛ (Amharic) Amharic NT Revised Amharic Bible in XML (2003). Printed version by United Bible Societies (C)1962. E-Text in transliterated ASCII format by Lapsley/Brooks Foundation 1994. Unicode UTF-8 transformation and XML-tagging by Dirk Röckmann 2003 ( www.nt-text.net ). With kind permission of the Bible Society of Ethiopia. Every non-commercial work using this data in any form must fully include this copyright statement! Every commercial use of parts or the complete data in any form needs written permission of the Bible Society of Ethiopia! 2014-09-09
Fonte: http://ebible.org/amh/ · eBible.org