Nations Bible

Lucas 19

መጽሐፍ ቅዱስ · Toca un versículo para ver sus referencias cruzadas.

1ኢየሱስንም የትኛው እንደ ሆነ ሊያይ ይፈልግ ነበር፤ ቁመቱም አጭር ነበረና ስለ ሕዝቡ ብዛት አቃተው። 4በዚያችም መንገድ ያልፍ ዘንድ አለውና ያየው ዘንድ ወደ ፊት ሮጦ በአንድ ሾላ ላይ ወጣ። 5ኢየሱስም ወደዚያ ስፍራ በደረሰ ጊዜ፥ አሻቅቦ አየና። ዘኬዎስ ሆይ፥ ዛሬ በቤትህ እውል ዘንድ ይገባኛልና ፈጥነህ ውረድ አለው። 6ፈጥኖም ወረደ በደስታም ተቀበለው። 7ሁሉም አይተው። ከኃጢአተኛ ሰው ጋር ሊውል ገባ ብለው አንጐራጐሩ። 8ዘኬዎስ ግን ቆሞ ጌታን። ጌታ ሆይ፥ ካለኝ ሁሉ እኵሌታውን ለድሆች እሰጣለሁ፤ ማንንም በሐሰት ከስሼ እንደ ሆንሁ አራት እጥፍ እመልሳለሁ አለው። 9ኢየሱስም። እርሱ ደግሞ የአብርሃም ልጅ ነውና ዛሬ ለዚህ ቤት መዳን ሆኖለታል፤ 10የሰው ልጅ የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን መጥቶአለና አለው። 11እነርሱም ይህን ሲሰሙ፥ ወደ ኢየሩሳሌም መቅረቡ ስለ ሆነ የእግዚአብሔርም መንግሥት ፈጥኖ ሊገለጥ እንዳለው ስለ መሰላቸው ምሳሌ ጭምር ተናገረ። 12ስለዚህም እንዲህ አላቸው። አንድ መኰንን ለራሱ መንግሥትን ይዞ ሊመለሰ ወደ ሩቅ አገር ሄደ። 13አሥር ባሪያዎችንም ጠርቶ አሥር ምናን ሰጣቸውና። እስክመጣ ድረስ ነግዱ አላቸው። 14የአገሩ ሰዎች ግን ይጠሉት ነበርና። ይህ በላያችን ሊነግሥ አንወድም ብለው በኋላው መልክተኞችን ላኩ። 15መንግሥትንም ይዞ በተመለሰ ጊዜ፥ ገንዘብ የሰጣቸውን እነዚህን ባሪያዎች ነግደው ምን ያህል እንዳተረፉ ያውቅ ዘንድ እንዲጠሩለት አዘዘ። 16የፊተኛውም ደርሶ። ጌታ ሆይ፥ ምናንህ አሥር ምናን አተረፈ አለው። 17እርሱም። መልካም፥ አንተ በጎ ባሪያ፥ በጥቂት የታመንህ ስለ ሆንህ በአሥር ከተማዎች ላይ ሥልጣን ይሁንልህ አለው። 18ሁለተኛውም መጥቶ። ጌታ ሆይ፥ ምናንህ አምስት ምናን አተረፈ አለው። 19ይህንም ደግሞ። አንተም በአምስት ከተማዎች ላይ ሁን አለው። 20ሌላውም መጥቶ። ጌታ ሆይ፥ በጨርቅ ጠቅልዬ የጠበቅኋት ምናንህ እነሆ፤ 21ፈርቼሃለሁና፥ ጨካኝ ሰው ስለ ሆንህ፤ ያላኖርኸውን ትወስዳለህ ያልዘራኸውንም ታጭዳለህ አለው። 22እርሱም። አንተ ክፉ ባሪያ፥ አፍህ በተናገረው እፈርድብሃለሁ። እኔ ያላኖርሁትን የምወስድና ያልዘራሁትን የማጭድ ጨካኝ ሰው እንደ ሆንሁ አወቅህ፤ ምን ነው ገንዘቤን ለለዋጮች አደራ ያልሰጠኸው? 23እኔም መጥቼ ከትርፉ ጋር እወስደው ነበር አለው። 24በዚያም ቆመው የነበሩትን። ምናኑን ውሰዱበት አሥሩ ምናን ላለውም ስጡት አላቸው። 25እነርሱም። ጌታ ሆይ፥ አሥር ምናን አለው አሉት። 26እላችኋለሁ፥ ላለው ሁሉ ይሰጠዋል፥ ከሌለው ግን ያው ያለው ስንኳ ይወሰድበታል። 27ነገር ግን እነዚያን በላያቸው ልነግሥ ያልወደዱትን ጠላቶቼን ወደዚህ አምጡአቸው በፊቴም እረዱአቸው። 28ይህንም ከተናገረ በኋላ፥ ወደ ኢየሩሳሌም ሲወጣ ይቀድማቸው ነበር። 29ደብረ ዘይትም በሚባል ተራራ አጠገብ ወዳሉት ወደ ቤተ ፋጌና ወደ ቢታንያ በቀረበ ጊዜ፥ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለቱን ላከና። 30በፊታችሁ ወዳለችው መንደር ሂዱ፥ ወደ እርስዋም ገብታችሁ ከሰው ማንም ገና ያልተቀመጠበት ውርንጫ ታስሮ ታገኛላችሁ፥ ፈትታችሁም አምጡት። 31ማንም። ስለ ምን ትፈቱታላችሁ? ብሎ ቢጠይቃችሁ፥ እንዲሁ። ለጌታ ያስፈልገዋል በሉ አላቸው። 32የተላኩትም ሄደው እንዳላቸው አገኙ። 33እነርሱም ውርንጫውን ሲፈቱ ጌቶቹ። ውርንጫውን ስለ ምን ትፈቱታላችሁ? አሉአቸውም 34እነርሱም። ለጌታ ያስፈልገዋል አሉ። 35ወደ ኢየሱስም አመጡት፥ በውርንጫውም ላይ ልብሳቸውን ጭነው ኢየሱስን አስቀመጡት። 36ሲሄድም ልብሳቸውን በመንገድ ያነጥፉ ነበር። 37ወደ ደብረ ዘይት ቍልቍለትም አሁን በቀረበ ጊዜ፥ ደቀ መዛሙርቱ ሁላቸው ደስ እያላቸው ተአምራትን ሁሉ ስላዩ በታላቅ ድምፅ እግዚአብሔርን ሊያመሰግኑ ጀምረው። 38በጌታ ስም የሚመጣ ንጉሥ የተባረከ ነው፤ በሰማይ ሰላም በአርያምም ክብር አሉ። 39ከሕዝብም መካከል ከፈሪሳውያን አንዳንዱ። መምህር ሆይ፥ ደቀ መዛሙርትህን ገሥጻቸው አሉት። 40መልሶም። እላችኋለሁ፥ እነዚህ ዝም ቢሉ ድንጋዮች ይጮኻሉ አላቸው። 41ሲቀርብም ከተማይቱን አይቶ አለቀሰላት፥ 42እንዲህ እያለ። ለሰላምሽ የሚሆነውን በዚህ ቀን አንቺስ ስንኳ ብታውቂ፤ አሁን ግን ከዓይንሽ ተሰውሮአል። 43ወራት ይመጣብሻልና፥ ጠላቶችሽም ቅጥር ይቀጥሩብሻል ይከቡሻልም በየበኵሉም ያስጨንቁሻል፤ 44አንቺንም በአንቺም ውስጥ የሚኖሩትን ልጆችሽን ወደ ታች ይጥላሉ፥ በአንቺ ውስጥም ድንጋይ በድንጋይ ላይ አይተዉም፥ የመጐብኘትሽን ዘመን አላወቅሽምና። 45ወደ መቅደስም ገብቶ በእርሱ የሚሸጡትን የሚገዙትንም ያወጣ ጀመር፤ 46እርሱም። ቤቴ የጸሎት ቤት ይሆናል ተብሎ ተጽፎአል፤ እናንተ ግን የወንበዴዎች ዋሻ አደረጋችሁት አላቸው። 47ዕለት ዕለትም በመቅደስ ያስተምር ነበር፤ ነገር ግን የካህናት አለቆችና ጻፎች የሕዝቡ ታላላቆችም ሊገድሉት ይፈልጉ ነበር፥ 48የሚያደርጉበትንም አጡ፤ ሕዝቡ ሁሉ ሲሰሙት ተንጠልጥለውበት ነበርና።

Ilustración artística: una interpretación, no un registro histórico.

¿Sabías que…?

De Jericó a Jerusalén

  • Zaqueo, jefe de los recaudadores de impuestos y hombre muy rico, es descrito como superintendente de aduanas en Jericó. La ciudad producía y exportaba entonces una cantidad considerable de bálsamo, de modo que el puesto de aduanas era importante y explicaría su riqueza. Jericó, “lugar de fragancia”, era una ciudad amurallada en un vasto bosque de palmeras en la llanura del Jordán, a unas cinco millas al oeste del río.Fuentes: Zacchaeus · Jericho · el propio texto bíblico
  • Al subir desde Jericó, Jesús se acercó a Betfagé y Betania, en el monte de los Olivos, en el camino entre las dos ciudades. Betania, a unas dos millas al este de Jerusalén, en la ladera sureste de la sierra, debía su nombre a las muchas palmeras que crecían allí; Betfagé, “casa del higo verde”, estaba cerca y marcaba el límite de un camino de sábado desde Jerusalén, dos mil codos. El monte de los Olivos toma su nombre de los olivos de sus laderas y se alza al este de Jerusalén, al otro lado del valle de Cedrón.Fuentes: Bethphage · Bethany · Mount of Olives · el propio texto bíblico
  • Al acercarse y ver la ciudad, Jesús lloró y lamentó que Jerusalén no hubiera conocido, aquel día, lo que le traería paz. El nombre se explica como “posesión de paz” o “fundamento de paz”; en el original tiene forma dual, probablemente en referencia a los dos montes sobre los que fue edificada la ciudad, Sion y Moria, o, como algunos suponen, a la ciudad alta y la ciudad baja. Se la describe como una ciudad de montaña entronizada en una fortaleza montañosa.Fuentes: Jerusalem · el propio texto bíblico

Notas escritas con ayuda de IA a partir de fuentes abiertas (Theographic Bible Metadata, CC BY-SA 4.0; Easton’s Bible Dictionary, dominio público) y revisadas antes de publicarse.

Lugares de este capítulo

  • Jericho · Hoy: Tell el Alayiq · 31.852, 35.436 · versículo 1
  • Jerusalem · 31.777, 35.234 · versículos 11, 28, 41
  • Mount of Olives · 31.778, 35.246 · versículos 29, 37

Solo aparecen lugares identificados con alta confianza (90 % o más según las fuentes académicas reunidas por OpenBible). Mapa de la época: DARE (Digital Atlas of the Roman Empire), CC BY 4.0; mapa actual: © colaboradores de OpenStreetMap; lugares: OpenBible.info (CC BY 4.0).

Créditos y licencia de esta traducción
መጽሐፍ ቅዱስ
The New Testament in the Amharic language of Ethiopia
copyright © 1962, 2003 United Bible Societies
Language: አማርኛ (Amharic)
Amharic NT
Revised Amharic Bible in XML (2003).
Printed version by United Bible Societies (C)1962.
E-Text in transliterated ASCII format by Lapsley/Brooks Foundation 1994.
Unicode UTF-8 transformation and XML-tagging by Dirk Röckmann 2003 ( www.nt-text.net ).
With kind permission of the Bible Society of Ethiopia.
Every non-commercial work using this data in any form must fully include this copyright statement!
Every commercial use of parts or the complete data in any form needs written permission of the Bible Society of Ethiopia!
2014-09-09

Fuente: http://ebible.org/amh/ · eBible.org

Habla con nosotros

Cuéntanos desde dónde lees, cómo te ha ayudado la Biblia o qué podemos mejorar. Leemos todos los mensajes.