Hechos 20
መጽሐፍ ቅዱስ · Toca un versículo para ver sus referencias cruzadas.
1ሁከቱም ከቀረ በኋላ ጳውሎስ ደቀ መዛሙርቱን አስመጥቶ መከራቸው፥ ተሰናብቶአቸውም ወደ መቄዶንያ ይሄድ ዘንድ ወጣ። 2ያንም አገር እያለፈ በብዙ ቃል ከመከራቸው በኋላ ወደ ግሪክ አገር መጣ። 3በዚያም ሦስት ወር ተቀምጦ ወደ ሶርያ በመርከብ ሊሄድ ባሰበ ጊዜ፥ አይሁድ ሴራ ስላደረጉበት በመቄዶንያ አልፎ ይመለስ ዘንድ ቆረጠ። 4የሸኙትም የቤርያው ሱሲጳጥሮስ ከተሰሎንቄ ሰዎችም አርስጥሮኮስና ሲኮንዱስ የደርቤኑም ጋይዮስና ጢሞቴዎስ የእስያ ሰዎችም ቲኪቆስ ጥሮፊሞስም ነበሩ፤ 5እነዚህም ወደ ፊታችን አልፈው በጢሮአዳ ቆዩን። 6እኛ ግን ከቂጣ በዓል ቀን በኋላ ከፊልጵስዩስ በመርከብ ተነሥተን በአምስት ቀን ወደ ጢሮአዳ ወደ እነርሱ ደረስንና በዚያ ሰባት ቀን ተቀመጥን። 7ከሳምንቱም በመጀመሪያ ቀን እንጀራ ለመቁረስ ተሰብስበን ሳለን፥ ጳውሎስ በነገው ሊሄድ ስላሰበ ከእነርሱ ጋር ይነጋገር ነበር፥ እስከ መንፈቀ ሌሊትም ነገሩን አስረዘመ። 8ተሰብስበንም በነበርንበት ሰገነት እጅግ መብራት ነበረ። 9አውጤኪስ የሚሉትም አንድ ጎበዝ በመስኮት ተቀምጦ ታላቅ እንቅልፍ አንቀላፍቶ ነበር፤ ጳውሎስም ነገርን ባስረዘመ ጊዜ እንቅልፍ ከብዶት ከሦስተኛው ደርብ ወደ ታች ወደቀ፥ ሞቶም አነሡት። 10ጳውሎስም ወርዶ በላዩ ወደቀ፥ አቅፎም። ነፍሱ አለችበትና አትንጫጩ አላቸው። 11ወጥቶም እንጀራ ቆርሶም በላ፤ ብዙ ጊዜም እስኪነጋ ድረስ ተነጋገረ እንዲህም ሄደ። 12ብላቴናውንም ደኅና ሆኖ ወሰዱት እጅግም ተጽናኑ። 13እኛ ግን ጳውሎስን ከዚያ እንቀበለው ዘንድ ስላለን ወደ መርከብ ቀድመን ሄድንና ወደ አሶን ተነሣን፤ እርሱ በመሬት ይሄድ ዘንድ ስላሰበ እንደዚህ አዞ ነበርና። 14በአሶንም ባገኘን ጊዜ ተቀብለነው ወደ ሚጢሊኒ መጣን፤ 15በማግሥቱም ከዚያ በባሕር ተነሥተን በኪዩ ፊት ለፊት ደረስን፥ በነገውም ወደ ሳሞን ተሻገርን በትሮጊሊዮም አድረን በማግሥቱ ወደ ሚሊጢን መጣን። 16ጳውሎስ በእስያ እጅግ እንዳይቀመጥ ኤፌሶንን ይተው ዘንድ ቆርጦ ነበርና ቢቻለውም በዓለ ኀምሳን በኢየሩሳሌም ይውል ዘንድ ይቸኩል ነበርና። 17ከሚሊጢንም ወደ ኤፌሶን ልኮ የቤተክርስቲያንን ሽማግሌዎች አስጠራቸው፤ 18አሁንም፥ እነሆ፥ እኔ በመንፈስ ታስሬ ወደ ኢየሩሳሌም እሄዳለሁ፥ በዚያም የሚያገኘኝ ምን እንደ ሆነ አላውቅም፤ 23ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ። እስራትና መከራ ይቆይሃል ብሎ በየከተማው ሁሉ ይመሰክርልኛል። 24ነገር ግን ሩጫዬንና ከጌታ ከኢየሱስ የተቀበልሁትን አገልግሎት እርሱም የእግዚአብሔርን ጸጋ ወንጌልን መመስከር እፈጽም ዘንድ ነፍሴን በእኔ ዘንድ እንደማትከብር እንደ ከንቱ ነገር እቆጥራለሁ። 25አሁንም፥ እነሆ፥ እኔ የእግዚአብሔርን መንግሥት እየሰበክሁ በመካከላችሁ የዞርሁ ሁላችሁ ከእንግዲህ ወዲህ ፊቴን እንዳትዩ አውቃለሁ። 26ስለዚህ እኔ ከሰው ሁሉ ደም ንጹሕ እንደ ሆንሁ ዛሬ በዚች ቀን እመሰክርላችኋለሁ። 27የእግዚአብሔርን ምክር ሁሉ ነግሬአችኋለሁና፥ ምንም አላስቀረሁባችሁም። 28በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ። 29ስለዚህ ሦስት ዓመት ሌሊትና ቀን በእንባ እያንዳንዳችሁን ከመገሠጽ እንዳላቋረጥሁ እያሰባችሁ ትጉ። 32አሁንም ለእግዚአብሔርና ያንጻችሁ ዘንድ በቅዱሳንም ሁሉ መካከል ርስትን ይሰጣችሁ ዘንድ ለሚችል ለጸጋው ቃል አደራ ሰጥቻችኋለሁ። 33ከማንም ብር ወይም ወርቅ ወይም ልብስ አልተመኘሁም፤ 34እነዚህ እጆቼ በሚያስፈልገኝ ነገር ለእኔና ከእኔ ጋር ላሉት እንዳገለገሉ እናንተ ታውቃላችሁ። 35እንዲሁ እየደከማችሁ ድውዮችን ልትረዱና እርሱ ራሱ። ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው እንዳለ የጌታን የኢየሱስን ቃል ልታስቡ ይገባችሁ ዘንድ በሁሉ አሳየኋችሁ። 36ይህንም ብሎ ተንበርክኮ ከሁላቸው ጋር ጸለየ። 37ሁሉም እጅግ አለቀሱ፥ ጳውሎስንም አንገቱን አቅፈው ይስሙት ነበር፤ 38ይልቁንም። ከእንግዲህ ወዲህ ፊቴን አታዩም ስላላቸው ነገር እጅግ አዘኑ። እስከ መርከብም ድረስ ሸኙት።

¿Sabías que…?
Despedida camino a Jerusalén
- Al salir de Troas, Pablo envió a sus compañeros por delante en el barco y caminó hasta Assos por el camino romano. Assos era un puerto de la Asia proconsular, en Misia, en la costa norte del golfo de Adramitio; el trayecto a pie era de unas 20 millas, el de mar de unas 30, y la isla de Lesbos quedaba a unas 7 millas de la costa.Fuentes: el propio texto bíblico · Assos
- Pablo pasó de largo frente a Éfeso para no demorarse en la provincia de Asia —la provincia romana del oeste de Asia Menor, cuya capital era Éfeso—, porque esperaba, si era posible, llegar a Jerusalén para el día de Pentecostés. Se detuvo en Mileto, un puerto y la antigua capital de Jonia, a unas 36 millas al sur de Éfeso, y mandó llamar a los ancianos de la iglesia de Éfeso.Fuentes: el propio texto bíblico · Asia · Miletus
- Siete hombres viajaban con él: Sópater de Berea, Aristarco y Segundo de Tesalónica, Gayo de Derbe, Timoteo, y Tíquico y Trófimo de Asia. Aristarco, de Tesalónica, más tarde compartió el encarcelamiento de Pablo en Roma, y Trófimo, efesio, lo acompañó en esta parte del viaje y estuvo con él en Jerusalén.Fuentes: el propio texto bíblico · Aristarchus · Trophimus
Notas escritas con ayuda de IA a partir de fuentes abiertas (Theographic Bible Metadata, CC BY-SA 4.0; Easton’s Bible Dictionary, dominio público) y revisadas antes de publicarse.
Lugares de este capítulo
- Macedonia · 41.600, 22.540 · versículos 1, 3, 6
- Greece · 37.972, 23.727 · versículo 2
- Syria · Hoy: Syria 2 · 33.511, 36.306 · versículo 3
- Asia · 38.400, 28.300 · versículos 4, 16, 18
- Berea · Hoy: Veria · 40.518, 22.200 · versículo 4
- Thessalonica · Hoy: Thessaloniki · 40.638, 22.946 · versículo 4
- Troas · Hoy: Alexandria Troas · 39.752, 26.159 · versículos 5, 6
- Philippi · 41.012, 24.285 · versículo 6
- Assos · 39.491, 26.337 · versículos 13, 14
- Mitylene · Hoy: ancient theater at Mitylene · 39.110, 26.547 · versículo 14
- Chios · 38.373, 26.137 · versículo 15
- Miletus · 37.531, 27.276 · versículos 15, 17
- Samos · 37.750, 26.833 · versículo 15
- Trogyllium · Hoy: Cape Mycale · 37.659, 27.003 · versículo 15
- Ephesus · 37.939, 27.341 · versículos 16, 17
- Jerusalem · 31.777, 35.234 · versículos 16, 22
Solo aparecen lugares identificados con alta confianza (90 % o más según las fuentes académicas reunidas por OpenBible). Mapa de la época: DARE (Digital Atlas of the Roman Empire), CC BY 4.0; mapa actual: © colaboradores de OpenStreetMap; lugares: OpenBible.info (CC BY 4.0).
Créditos y licencia de esta traducción
መጽሐፍ ቅዱስ The New Testament in the Amharic language of Ethiopia copyright © 1962, 2003 United Bible Societies Language: አማርኛ (Amharic) Amharic NT Revised Amharic Bible in XML (2003). Printed version by United Bible Societies (C)1962. E-Text in transliterated ASCII format by Lapsley/Brooks Foundation 1994. Unicode UTF-8 transformation and XML-tagging by Dirk Röckmann 2003 ( www.nt-text.net ). With kind permission of the Bible Society of Ethiopia. Every non-commercial work using this data in any form must fully include this copyright statement! Every commercial use of parts or the complete data in any form needs written permission of the Bible Society of Ethiopia! 2014-09-09
Fuente: http://ebible.org/amh/ · eBible.org