Hechos 15
መጽሐፍ ቅዱስ · Toca un versículo para ver sus referencias cruzadas.
1አንዳንዶችም ከይሁዳ ወረዱና። እንደ ሙሴ ሥርዓት ካልተገረዛችሁ ትድኑ ዘንድ አትችሉም ብለው ወንድሞችን ያስተምሩ ነበር። 2በእነርሱና በጳውሎስ በበርናባስም መካከል ብዙ ጥልና ክርክር በሆነ ጊዜ፥ ስለዚህ ክርክር ጳውሎና በርናባስ ከእነርሱም አንዳንዶች ሌሎች ሰዎች ወደ ሐዋርያት ወደ ሽማግሌዎችም ወደ ኢየሩሳሌም ይወጡ ዘንድ ተቈረጠ። 3ቤተ ክርስቲያኑም በመንገድ እየረዳቸው እነርሱ የአሕዛብን መመለስ እየተረኩ በፊንቄና በሰማርያ አለፉ፥ ወንድሞችንም ሁሉ እጅግ ደስ አሰኙአቸው። 4ወደ ኢየሩሳሌምም በደረሱ ጊዜ ቤተ ክርስቲያንና ሐዋርያት ሽማግሌዎችም ተቀበሉአቸው፥ እግዚአብሔርም ከእነርሱ ጋር ያደረገውን ሁሉ አወሩ። 5ከፈሪሳውያን ወገን ግን ያመኑት አንዳንዶቹ ተነሥተው። ትገርዙአቸው ዘንድና የሙሴን ሕግ እንዲጠብቁ ታዙአቸው ዘንድ ይገባል አሉ። 6ሐዋርያትና ሽማግሌዎችም ስለዚህ ነገር ለመማከር ተሰበሰቡ። 7ከብዙ ክርክርም በኋላ ጴጥሮስ ተነሥቶ እንዲህ አላቸው ወንድሞች ሆይ፥ አሕዛብ ከአፌ የወንጌልን ቃል ሰምተው ያምኑ ዘንድ እግዚአብሔር በመጀመሪያው ዘመን ከእናንተ እኔን እንደ መረጠኝ እናንተ ታውቃላችሁ። 8ልብንም የሚያውቅ አምላክ ለእኛ ደግሞ እንደ ሰጠን መንፈስ ቅዱስን በመስጠት መሰከረላቸው፤ 9ልባቸውንም በእምነት ሲያነጻ በእኛና በእነርሱ መካከል አንዳች አልለየም። 10እንግዲህ አባቶቻችንና እኛ ልንሸከመው ያልቻልነውን ቀንበር በደቀ መዛሙርት ጫንቃ ላይ በመጫን እግዚአብሔርን አሁን ስለ ምን ትፈታተናላችሁ? 11ነገር ግን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ እንደ እነርሱ ደግሞ እንድን ዘንድ እናምናለን። 12ሕዝቡም ሁሉ ዝም አሉ፥ በርናባስና ጳውሎስም እግዚአብሔር በእጃቸው በአሕዛብ መካከል ያደረገውን ምልክትና ድንቅ ሁሉ ሲተርኩላቸው ይሰሙ ነበር። 13እነርሱም ዝም ካሉ በኋላ ያዕቆብ እንዲህ ብሎ መለሰ። ወንድሞች ሆይ፥ ስሙኝ። 14እግዚአብሔር ለስሙ የሚሆንን ወገን ከአሕዛብ ይወስድ ዘንድ አስቀድሞ እንዴት እንደ ጐበኘ ስምዖን ተርኮአል። 15ከዚህም ጋር የነቢያት ቃል ይሰማማል፥ እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ። 16ከጥንት ጀምሮ ሥራው ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ የታወቀ ነው። 19ስለዚህ ከአሕዛብ ወደ እግዚአብሔር የዞሩትን እንዳናስቸግራቸው፥ 20ነገር ግን ከጣዖት ርኵሰትና ከዝሙት ከታነቀም ከደምም ይርቁ ዘንድ እንድንጽፍላቸው እቈርጣለሁ። 21ሙሴስ ከቀደሙት ትውልድ ጀምሮ በሰንበት በሰንበት በምኵራቦቹ ሲያነቡ በየከተማው እርሱን የሚሰብኩ አሉት። 22ያን ጊዜ ሐዋርያትና ሽማግሌዎች ከቤተ ክርስቲያኑ ሁሉ ጋር ከእነርሱ የተመረጡትን ሰዎች ከጳውሎስና ከበርናባስ ጋር ወደ አንጾኪያ ይልኩ ዘንድ ፈቀዱ፤ እነርሱም በወንድሞች መካከል ዋናዎች ሆነው በርስያን የተባለው ይሁዳና ሲላስ ነበሩ። 23እንዲህም ጽፈው በእነርሱ እጅ ላኩ። ሐዋርያትና ሽማግሌዎች ወንድሞችም በአንጾኪያና በሶርያ በኪልቅያም ለሚኖሩ ከአሕዛብ ወገን ለሆኑ ወንድሞች ሰላምታ ያቀርባሉ። 24ያላዘዝናቸው ሰዎች ከእኛ ወጥተው። ትገረዙ ዘንድና ሕግን ትጠብቁ ዘንድ ይገባችኋል ብለው ልባችሁን እያወኩ በቃል እንዳናወጡአችሁ ስለ ሰማን፥ 25ራሳቸውም ደግሞ በቃላቸው ያንኑ ይነግሩአችሁ ዘንድ ይሁዳንና ሲላስን ልከናል። 28እነርሱም ተሰናብተው ወደ አንጾኪያ ወረዱ፥ ሕዝቡንም ሰብስበው ደብዳቤውን ሰጡአቸው። 31ባነበቡትም ጊዜ ከምክሩ የተነሣ ደስ አላቸው። 32ይሁዳና ሲላስም ደግሞ ነቢያት ነበሩና ወንድሞችን በብዙ ቃል መክረው አጸኑአቸው። 33አያሌ ቀንም ከተቀመጡ በኋላ ከወንድሞች በሰላም ተሰናብተው ወደ ሐዋርያት ሄዱ። 34ሲላስ ግን በዚያ ይኖር ዘንድ ፈቀደ። 35ጳውሎስና በርናባስም ከሌሎች ከብዙ ሰዎች ጋር ደግሞ የጌታን ቃል እያስተማሩና ወንጌልን እየሰበኩ በአንጾኪያ ይቀመጡ ነበር። 36ከጥቂት ቀንም በኋላ ጳውሎስ በርናባስን። ተመልሰን የጌታን ቃል በተናገርንበት በየከተማው ሁሉ ወንድሞችን እንጐብኛቸው፥ እንዴት እንዳሉም እንወቅ አለው። 37በርናባስም ማርቆስ የተባለውን ዮሐንስን ደግሞ ከእነርሱ ጋር ይወስድ ዘንድ አሰበ፤ 38ጳውሎስ ግን ይህን ከእነርሱ ጋር ሊወስድ አልፈቀደም፥ ከእነርሱ ዘንድ ከጵንፍልያ ተለይቶ ነበርና፥ ወደ ሥራም ከእነርሱ ጋር አልመጣም ነበርና። 39ስለዚህም እርስ በርሳቸው እስኪለያዩ ድረስ መከፋፋት ሆነ፥ በርናባስም ማርቆስን ይዞ በመርከብ ወደ ቆጵሮስ ሄደ። 40ጳውሎስ ግን ሲላስን መረጠ፥ ወንድሞችም ለእግዚአብሔር ጸጋ አደራ ከሰጡት በኋላ ወጣ፤ 41አብያተ ክርስትያናትንም እያጸና በሶርያና በኪልቅያ ይዞር ነበር።

¿Sabías que…?
El concilio sobre los creyentes gentiles
- La controversia comenzó en Antioquía, a orillas del Orontes, unas trescientas millas al norte de Jerusalén, ciudad que entonces ocupaba el tercer lugar entre las ciudades del Imperio romano, después de Roma y Alejandría. De camino al concilio, Pablo y Bernabé pasaron por Fenicia, una franja costera de unas ciento veinte millas, y por Samaria. Una nota cronológica fecha el Concilio de Jerusalén en el año 46 d. C.Fuentes: Antioch (Syria) · Phenicia · el propio texto bíblico · Jerusalem Council
- El Easton's Bible Dictionary (1897) afirma que Santiago, a quien llama hermano o pariente cercano de Jesús, dirigía la iglesia en Jerusalén y presidió el concilio sobre los gentiles. La carta que siguió iba dirigida a los creyentes gentiles de Antioquía, Siria y Cilicia. Cilicia, provincia de origen de Pablo y provincia marítima romana en el sureste de Asia Menor desde el 67 a. C., incluía su ciudad natal, Tarso.Fuentes: James (Brother of Jesus) · el propio texto bíblico · Cilicia · Paul
- Judas, llamado Barsabás, y Silas, también conocido como Silvano, eran profetas y hombres destacados de la iglesia de Jerusalén, enviados para confirmar en persona la decisión del concilio. Un desacuerdo posterior y agudo por Juan Marcos, primo de Bernabé, separó a los dos misioneros: Bernabé se llevó a Marcos y zarpó hacia Chipre, mientras Pablo eligió a Silas. Una nota cronológica fecha esa separación en el año 47 d. C.Fuentes: el propio texto bíblico · Silas · John Mark · Paul and Barnabas part ways
Notas escritas con ayuda de IA a partir de fuentes abiertas (Theographic Bible Metadata, CC BY-SA 4.0; Easton’s Bible Dictionary, dominio público) y revisadas antes de publicarse.
Lugares de este capítulo
- Antioch · Hoy: Antioch on the Orontes · 36.227, 36.172 · versículos 1, 22, 23, 30, 35
- Judea · Hoy: Judea 1 · 31.777, 35.234 · versículo 1
- Jerusalem · 31.777, 35.234 · versículos 2, 3, 4, 22, 23, 33
- Phoenicia · 33.271, 35.196 · versículo 3
- Samaria · Hoy: Samaria 2 · 32.276, 35.195 · versículo 3
- Cilicia · 36.913, 34.892 · versículos 23, 41
- Syria · Hoy: Syria 2 · 33.511, 36.306 · versículos 23, 41
- Pamphylia · 37.000, 31.000 · versículo 38
- Cyprus · 35.000, 33.000 · versículo 39
Solo aparecen lugares identificados con alta confianza (90 % o más según las fuentes académicas reunidas por OpenBible). Mapa de la época: DARE (Digital Atlas of the Roman Empire), CC BY 4.0; mapa actual: © colaboradores de OpenStreetMap; lugares: OpenBible.info (CC BY 4.0).
Créditos y licencia de esta traducción
መጽሐፍ ቅዱስ The New Testament in the Amharic language of Ethiopia copyright © 1962, 2003 United Bible Societies Language: አማርኛ (Amharic) Amharic NT Revised Amharic Bible in XML (2003). Printed version by United Bible Societies (C)1962. E-Text in transliterated ASCII format by Lapsley/Brooks Foundation 1994. Unicode UTF-8 transformation and XML-tagging by Dirk Röckmann 2003 ( www.nt-text.net ). With kind permission of the Bible Society of Ethiopia. Every non-commercial work using this data in any form must fully include this copyright statement! Every commercial use of parts or the complete data in any form needs written permission of the Bible Society of Ethiopia! 2014-09-09
Fuente: http://ebible.org/amh/ · eBible.org