Nations Bible

Mark 8

መጽሐፍ ቅዱስ · Tap a verse to see its cross-references.

1በዚያ ወራት ደግሞ ብዙ ሕዝብ ነበረ የሚበሉትም ስለሌላቸው ደቀ መዛሙርቱን ጠርቶ። 2ሕዝቡ ከእኔ ጋር እስካሁን ሦስት ቀን ውለዋልና የሚበሉት ስለሌላቸው አዝንላቸዋለሁ፤ 3ከእነርሱም አንዳንዶቹ ከሩቅ መጥተዋልና ጦማቸውን ወደ ቤታቸው ባሰናብታቸው በመንገድ ይዝላሉ አላቸው። 4ደቀ መዛሙርቱም። በዚህ በምድረ በዳ እንጀራ ከየት አግኝቶ ሰው እነዚህን ማጥገብ ይችላል? ብለው መለሱለት። 5እርሱም። ስንት እንጀራ አላችሁ? ብሎ ጠየቃቸው፥ እነርሱም። ሰባት አሉት። 6ሕዝቡም በምድር እንዲቀመጡ አዘዘ። ሰባቱንም እንጀራ ይዞ አመሰገነ፥ ቈርሶም እንዲያቀርቡላቸው ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠ፥ ለሕዝቡም አቀረቡ። 7ጥቂትም ትንሽ ዓሣ ነበራቸው፤ ባረከውም ይህንም ደግሞ እንዲያቀርቡላቸው አዘዘ። 8በሉም ጠገቡም፥ የተረፈውንም ቍርስራሽ ሰባት ቅርጫት አነሡ። 9የበሉትም አራት ሺህ ያህል ነበሩ። 10አሰናበታቸውም። ወዲያውም ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደ ታንኳይቱ ገብቶ ወደ ዳልማኑታ አገር መጣ። 11ፈሪሳውያንም ወጡና ሊፈትኑት ከሰማይ ምልክት ከእርሱ ፈልገው ከእርሱ ጋር ይከራከሩ ጀመር። 12በመንፈሱም እጅግ ቃተተና። ይህ ትውልድ ስለ ምን ምልክት ይፈልጋል? እውነት እላችኋለሁ፥ ለዚህ ትውልድ ምልክት አይሰጠውም አለ። 13ትቶአቸውም እንደ ገና ወደ ታንኳይቱ ገብቶ ወደ ማዶ ሄደ። 14እንጀራ መያዝም ረሱ፥ ለእነርሱም ከአንድ እንጀራ በቀር በታንኳይቱ አልነበራቸውም። 15እርሱም። ተጠንቀቁ፤ ከፈሪሳውያንና ከሄሮድስ እርሾ ተጠበቁ ብሎ አዘዛቸው። 16እርስ በርሳቸውም። እንጀራ ስለሌለን ይሆናል ብለው ተነጋገሩ። 17ኢየሱስም አውቆ እንዲህ አላቸው። እንጀራ ስለሌላችሁ ስለ ምን ትነጋገራላችሁ? ገና አልተመለከታችሁምን? አላስተዋላችሁምን? 18ልባችሁስ ደንዝዞአልን? ዓይን ሳላችሁ አታዩምን? ጆሮስ ሳላችሁ አትሰሙምን? ትዝስ አይላችሁምን? 19አምስቱን እንጀራ ለአምስት ሺህ በቈረስሁ ጊዜ፥ ቍርስራሹ የሞላ ስንት መሶብ አነሣችሁ? እነርሱም። አሥራ ሁለት አሉት። 20ሰባቱን እንጀራስ ለአራት ሺህ በቈረስሁ ጊዜ፥ ቍርስራሹ የሞላ ስንት ቅርጫት አነሣችሁ? እነርሱም። ሰባት አሉት። 21ገና አላስተዋላችሁምን? አላቸው። 22ወደ ቤተ ሳይዳም መጡ። ዕውርም አመጡለት፥ እንዲዳስሰውም ለመኑት። 23ዕውሩንም እጁን ይዞ ከመንደር ውጭ አወጣው፥ በዓይኑም ተፍቶበት እጁንም ጭኖበት። አንዳች ታያለህን ብሎ ጠየቀው። 24አሻቅቦም። ሰዎች እንደ ዛፍ ሲመላለሱ አያለሁ አለ። 25ከዚህም በኋላ ደግሞ እጁን በዓይኑ ላይ ጫነበት አጥርቶም አየና ዳነም ከሩቅም ሳይቀር ሁሉን ተመለከተ። 26ወደ ቤቱም ሰደደውና። ወደ መንደሩ አትግባ በመንደሩም ለማንም አንዳች አትናገር አለው። 27ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱም በፊልጶስ ቂሣርያ ወዳሉ መንደሮች ወጡ በመንገድም። ሰዎች እኔ ማን እንደ ሆንሁ ይላሉ? ብሎ ደቀ መዛሙርቱን ጠየቃቸው። 28እነርሱም። መጥምቁ ዮሐንስ፥ ሌሎችም ኤልያስ፥ ሌሎችም ከነቢያት አንዱ ብለው ነገሩት። 29እናንተስ እኔ ማን እንደ ሆንሁ ትላላችሁ? ብሎ ጠየቃቸው። ጴጥሮስም። አንተ ክርስቶስ ነህ ብሎ መለሰለት። 30ስለ እርሱም ለማንም እንዳይናገሩ አዘዛቸው። 31የሰው ልጅ ብዙ መከራ ሊቀበል፥ ከሽማግሌዎችም ከካህናት አለቆችም ከጻፎችም ሊጣል፥ ሊገደልም ከሦስት ቀንም በኋላ ሊነሣ እንዲገባው ያስተምራቸው ጀመር፤ ቃሉንም ገልጦ ይናገር ነበር። 32ጴጥሮስም ወደ እርሱ ወስዶ ይገሥጸው ጀመር። 33እርሱ ግን ዘወር አለ ደቀ መዛሙርቱንም አይቶ ጴጥሮስን ገሠጸውና። ወደ ኋላዬ ሂድ፥ አንተ ሰይጣን፤ የሰውን እንጂ የእግዚአብሔርን ነገር አታስብምና አለው። 34ሕዝቡንም ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ጠርቶ እንዲህ አላቸው። በኋላዬ ሊመጣ የሚወድ ቢኖር፥ ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ። 35ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ሁሉ ያጠፋታልና፥ ስለ እኔና ስለ ወንጌል ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ ግን ያድናታል። 36ሰው ዓለምን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል? 37ሰውስ ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል? 38በዚህም በዘማዊና በኃጢአተኛ ትውልድ መካከል በእኔና በቃሌ የሚያፍር ሁሉ፥ የሰው ልጅ ደግሞ በአባቱ ክብር ከቅዱሳን መላእክት ጋር በመጣ ጊዜ በእርሱ ያፍርበታል።

Artistic illustration — an interpretation, not a historical record.

Did you know?

Seeing Who Jesus Is

  • After about four thousand men had eaten and seven baskets of broken pieces had been picked up, Jesus got into the boat with his disciples and went to the district of Dalmanutha, a name that appears only in this chapter. It was a place on the west side of the Sea of Galilee, near Magdala. In the parallel passage in Matthew, he comes into the borders of Magdala, which was probably the Greek name of one of the watch-towers on the western shore of the lake.Sources: the Bible text itself · Dalmanutha
  • At Bethsaida some people brought a blind man, and Jesus led him by the hand out of the village, spit on his eyes, and placed his hands on him. At first the man saw people like trees walking; only when Jesus placed his hands on the man’s eyes again was his sight fully restored. The town is described as standing on the east side of the lake, about two miles up the Jordan, in Gaulonitis; Philip the tetrarch enlarged it and called it Julias, after the emperor’s daughter, though some have supposed there was only one Bethsaida, built on both sides of the lake near where the Jordan enters it.Sources: the Bible text itself · Bethsaida
  • Jesus and his disciples went on to the villages around Caesarea Philippi, a city about twenty miles north of the Sea of Galilee, near the base of Mount Hermon at the upper source of the Jordan, and described as the northern limit of his public ministry. According to some, it had earlier been Baal-Gad or Baal-Hermon, a Canaanite sanctuary of Baal, and it was later called Panium or Paneas, from a deep cavern full of water near the town. There Peter said, "You are the Christ," and when he rebuked Jesus for teaching that the Son of Man must suffer many things, be killed, and rise after three days, Jesus answered, "Get behind me, Satan," a name that means adversary or accuser.Sources: the Bible text itself · Caesarea Philippi · Satan

Notes written with AI assistance from open sources (Theographic Bible Metadata, CC BY-SA 4.0; Easton’s Bible Dictionary, public domain) and reviewed before publishing.

Places in this chapter

  • Caesarea Philippi · Today: Banias · 33.246, 35.693 · verse 27
  • Galilee · 32.760, 35.527 · verse 27

Only places identified with high confidence are shown (90% or more according to the scholarly sources compiled by OpenBible). Period map: DARE (Digital Atlas of the Roman Empire), CC BY 4.0; modern map: © OpenStreetMap contributors; places: OpenBible.info (CC BY 4.0).

Credits and license for this translation
መጽሐፍ ቅዱስ
The New Testament in the Amharic language of Ethiopia
copyright © 1962, 2003 United Bible Societies
Language: አማርኛ (Amharic)
Amharic NT
Revised Amharic Bible in XML (2003).
Printed version by United Bible Societies (C)1962.
E-Text in transliterated ASCII format by Lapsley/Brooks Foundation 1994.
Unicode UTF-8 transformation and XML-tagging by Dirk Röckmann 2003 ( www.nt-text.net ).
With kind permission of the Bible Society of Ethiopia.
Every non-commercial work using this data in any form must fully include this copyright statement!
Every commercial use of parts or the complete data in any form needs written permission of the Bible Society of Ethiopia!
2014-09-09

Source: http://ebible.org/amh/ · eBible.org

Talk to us

Tell us where you read from, how the Bible has helped you, or what we could improve. We read every message.