Matthew 4
መጽሐፍ ቅዱስ · Tap a verse to see its cross-references.
1ከዚያ ወዲያ ኢየሱስ ከዲያብሎስ ይፈተን ዘንድ መንፈስ ወደ ምድረ በዳ ወሰደው፥ 2አርባ ቀንና አርባ ሌሊትም ከጦመ በኋላ ተራበ። 3ፈታኝም ቀርቦ። የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ፥ እነዚህ ድንጋዮች እንጀራ እንዲሆኑ በል አለው። 4እርሱም መልሶ። ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፎአል አለው። 5ከዚህ በኋላ ዲያቢሎስ ወደ ቅድስት ከተማ ወሰደውና እርሱን በመቅደስ ጫፍ ላይ አቁሞ። 6መላእክቱን ስለ አንተ ያዝልሃል እግርህንም በድንጋይ ከቶ እንዳትሰናከል በእጃቸው ያነሡሃል ተብሎ ተጽፎአልና የእግዚአብሔር ልጅስ ከሆንህ፥ ወደ ታች ራስህን ወርውር አለው። 7ኢየሱስም። ጌታን አምላክህን አትፈታተነው ተብሎ ደግሞ ተጽፎአል አለው። 8ደግሞ ዲያቢሎስ እጅግ ረጅም ወደ ሆነ ተራራ ወሰደው፥ የዓለምንም መንግሥታት ሁሉ ክብራቸውንም አሳይቶ። 9ወድቀህ ብትሰግድልኝ ይህን ሁሉ እሰጥሃለሁ አለው። 10ያን ጊዜ ኢየሱስ። ሂድ፥ አንተ ሰይጣን ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ ተብሎ ተጽፎአልና አለው። 11ያን ጊዜ ዲያቢሎስ ተወው፥ እነሆም፥ መላእክት ቀርበው ያገለግሉት ነበር። 12ኢየሱስም ዮሐንስ አልፎ እንደ ተሰጠ በሰማ ጊዜ ወደ ገሊላ ፈቀቅ ብሎ ሄደ። 13ናዝሬትንም ትቶ በዛብሎንና በንፍታሌም አገር በባሕር አጠገብ ወደ አለችው ወደ ቅፍርናሆም መጥቶ ኖረ። 14የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሆነ። ከዚያ ዘመን ጀምሮ ኢየሱስ። መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ እያለ ይሰብክ ጀመር። 18በገሊላ ባሕር አጠገብ ሲመላለስም ሁለት ወንድማማች ጴጥሮስ የሚሉትን ስምዖንን ወንድሙንም እንድርያስን መረባቸውን ወደ ባሕር ሲጥሉ አየ፥ ዓሣ አጥማጆች ነበሩና። 19እርሱም። በኋላዬ ኑና ሰዎችን አጥማጆች እንድትሆኑ አደርጋችኋለሁ አላቸው። 20ወዲያውም መረባቸውን ትተው ተከተሉት። 21ከዚያም እልፍ ብሎ ሌሎችን ሁለት ወንድማማች የዘብዴዎስን ልጅ ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ከአባታቸው ከዘብዴዎስ ጋር በታንኳ መረባቸውን ሲያበጁ አየ፤ ጠራቸውም። 22እነርሱም ወዲያው ታንኳይቱንና አባታቸውን ትተው ተከተሉት። 23ኢየሱስም በምኩራቦቻቸው እያስተማረ የመንግሥትንም ወንጌል እየሰበከ በሕዝብም ያለውን ደዌና ሕማም ሁሉ እየፈወሰ በገሊላ ሁሉ ይዞር ነበር። 24ዝናውም ወደ ሶርያ ሁሉ ወጣ፤ በልዩ ልዩ ደዌና ሥቃይም ተይዘው የታመሙትን ሁሉ አጋንንትም ያደሩባቸውን በጨረቃም የሚነሣባቸውን ሽባዎችንም ወደ እርሱ አመጡ፥ ፈወሳቸውም። 25ከገሊላም ከአሥሩ ከተማም ከኢየሩሳሌምም ከይሁዳም ከዮርዳኖስም ማዶ ብዙ ሕዝብ ተከተሉት።

Did you know?
From the Wilderness to the Shores of Galilee
- The tempter in this chapter is called both the devil and Satan, a name meaning "adversary" or "accuser." A Bible dictionary notes that in the New Testament Satan is used interchangeably with the devil, and that he tempted Jesus in the wilderness. After fasting forty days and forty nights, Jesus refused demands to turn stones into bread, to throw himself from the pinnacle of the temple, and to worship Satan in exchange for the kingdoms of the world, answering from Scripture until the devil left and angels ministered to him.Sources: the Bible text itself · Satan
- When Jesus heard that John had been imprisoned, he withdrew to Galilee, left Nazareth, and settled in Capernaum, by the sea in the region of Zebulun and Naphtali, a move that Matthew links to words spoken through the prophet Isaiah. A geographical note explains that Galilee remained long occupied by its earlier inhabitants and so came to be called "Galilee of the Gentiles." Capernaum is not mentioned in the Old Testament; a place entry says that after Jesus was expelled from Nazareth it became his own city.Sources: the Bible text itself · Galilee · Capernaum
- Walking beside the Sea of Galilee—a lake that the Gospel of John also calls the Sea of Tiberias, about twelve and a half miles long—Jesus called two pairs of brothers who worked as fishermen. Simon, called Peter, and Andrew were casting a net; a Bible dictionary notes that Andrew, from Bethsaida, had first been a disciple of John the Baptist, and that the two brothers did not become Jesus' stated attendants until after John's imprisonment. Farther along, James and John, sons of Zebedee, were in a boat with their father mending nets; Jesus called them, and both pairs left their work and followed him.Sources: the Bible text itself · Andrew · James (Son of Zebedee) · Sea of Galilee
Notes written with AI assistance from open sources (Theographic Bible Metadata, CC BY-SA 4.0; Easton’s Bible Dictionary, public domain) and reviewed before publishing.
Places in this chapter
- Jerusalem · 31.777, 35.234 · verses 5, 25
- Galilee · 32.760, 35.527 · verses 12, 13, 15, 23, 25
- Judea · Today: Judea 1 · 31.777, 35.234 · verses 12, 25
- Nazareth · 32.702, 35.298 · verse 13
- Jordan · Today: Jordan River · 31.761, 35.558 · verses 15, 25
- Sea of Galilee · 32.819, 35.590 · verse 18
- Syria · Today: Syria 2 · 33.511, 36.306 · verse 24
- Decapolis · 32.717, 35.800 · verse 25
Only places identified with high confidence are shown (90% or more according to the scholarly sources compiled by OpenBible). Period map: DARE (Digital Atlas of the Roman Empire), CC BY 4.0; modern map: © OpenStreetMap contributors; places: OpenBible.info (CC BY 4.0).
Credits and license for this translation
መጽሐፍ ቅዱስ The New Testament in the Amharic language of Ethiopia copyright © 1962, 2003 United Bible Societies Language: አማርኛ (Amharic) Amharic NT Revised Amharic Bible in XML (2003). Printed version by United Bible Societies (C)1962. E-Text in transliterated ASCII format by Lapsley/Brooks Foundation 1994. Unicode UTF-8 transformation and XML-tagging by Dirk Röckmann 2003 ( www.nt-text.net ). With kind permission of the Bible Society of Ethiopia. Every non-commercial work using this data in any form must fully include this copyright statement! Every commercial use of parts or the complete data in any form needs written permission of the Bible Society of Ethiopia! 2014-09-09
Source: http://ebible.org/amh/ · eBible.org