Nations Bible

2 Peter 2

መጽሐፍ ቅዱስ · Tap a verse to see its cross-references.

1ነገር ግን ሐሰተኞች ነቢያት ደግሞ በሕዝቡ መካከል ነበሩ እንዲሁም በመካከላችሁ ደግሞ ሐሰተኞች አስተማሪዎች ይሆናሉ፤ እነርሱም የዋጃቸውን ጌታ እንኳ ክደው የሚፈጥንን ጥፋት በራሳቸው ላይ እየሳቡ የሚያጠፋ ኑፋቄን አሹልከው ያገባሉ፤ 2ብዙዎችም በመዳራታቸው ይከተሉአቸዋል በእነርሱም ጠንቅ የእውነት መንገድ ይሰደባል። 3ገንዘብንም በመመኘት በተፈጠረ ነገር ይረቡባችኋል፤ ፍርዳቸውም ከጥንት ጀምሮ አይዘገይም ጥፋታቸውም አያንቀላፋም። 4እግዚአብሔር ኃጢአትን ላደረጉ መላእክት ሳይራራላቸው ወደ ገሃነም ጥሎ በጨለማ ጉድጓድ ለፍርድ ሊጠበቁ አሳልፎ ከሰጣቸው፥ 5ለቀደመውም ዓለም ሳይራራ ከሌሎች ሰባት ጋር ጽድቅን የሚሰብከውን ኖኅን አድኖ በኃጢአተኞች ዓለም ላይ የጥፋትን ውኃ ካወረደ፥ 6ኃጢአትንም ያደርጉ ዘንድ ላሉት ምሳሌ አድርጎ ከተማዎችን ሰዶምንና ገሞራን አመድ እስኪሆኑ ድረስ አቃጥሎና ገልብጦ ከፈረደባቸው፥ 7ዳሩ ግን መላእክት በኃይልና በብርታት ከእነርሱ ይልቅ ምንም ቢበልጡ በጌታ ፊት በእነርሱ ላይ የስድብን ፍርድ አያመጡም። 12እነዚህ ግን ለመጠመድና ለመጥፋት በፍጥረታቸው እንደ ተወለዱ አእምሮ እንደ ሌላቸው እንስሶች ሆነው፥ በማያውቁት ነገር እየተሳደቡ በጥፋታቸው ይጠፋሉ፤ 13የዓመፃቸውን ደመወዝ ይቀበላሉ። በቀን ሲዘፍኑ እንደ ተድላ ይቆጥሩታል፤ ነውረኞችና ርኵሳን ሆነው ከእናንተ ጋር ሲጋበዙ በፍቅር ግብዣ ይዘፍናሉ፤ 14ምንዝር የሞላባቸው ኃጢአትንም የማይተዉ ዓይኖች አሉአቸው፤ የማይጸኑትን ነፍሳት ያታልላሉ፤ መመኘትን የለመደ ልብ አላቸው፤ የተረገሙ ናቸው። 15ቅንን መንገድ ትተው ተሳሳቱ፤ የባሶርን ልጅ የበለዓምን መንገድ ተከተሉ፤ እርሱ የዓመፃን ደመወዝ ወደደ፥ 16ነገር ግን ስለ መተላለፉ ተዘለፈ፤ ቃል የሌለው አህያ በሰው ቃል ተናግሮ የነቢዩን እብድነት አገደ። 17ድቅድቅ ጨለማ ለዘላለም የተጠበቀላቸው እነዚህ ውኃ የሌለባቸው ምንጮች በዐውሎ ነፋስም የተነዱ ደመናዎች ናቸው። 18ከንቱና ከመጠን ይልቅ ታላቅ የሆነውን ቃል ይናገራሉና፥ በስሕተትም ከሚኖሩት አሁን የሚያመልጡትን በሥጋ ሴሰኛ ምኞት ያታልላሉ። 19ራሳቸው የጥፋት ባሪያዎች ሆነው። አርነት ትወጣላችሁ እያሉ ተስፋ ይሰጡአቸዋል፤ ሰው ለተሸነፈበት ለእርሱ ተገዝቶ ባሪያ ነውና። 20በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እውቀት ከዓለም ርኵሰት ካመለጡ በኋላ ዳግመኛ በእርስዋ ተጠላልፈው የተሸነፉ ቢሆኑ፥ ከፊተኛው ኑሮአቸው ይልቅ የኋለኛው የባሰ ሆኖባቸዋል። 21አውቀዋት ከተሰጣቸው ከቅድስት ትእዛዝ ከሚመለሱ የጽድቅን መንገድ ባላወቋት በተሻላቸው ነበርና። 22ውሻ ወደ ትፋቱ ይመለሳል፥ ደግሞ። የታጠበች እርያ በጭቃ ለመንከባለል ትመለሳለች እንደሚባል እውነተኞች ምሳሌዎች ሆኖባቸዋል።

Artistic illustration — an interpretation, not a historical record.

Did you know?

False Teachers and Past Judgments

  • 2 Peter points to Sodom and Gomorrah, reduced to ashes, as an example of what is coming on the ungodly. Easton's Bible Dictionary (1897) describes Sodom as a walled city in the vale of Siddim, destroyed by fire from heaven, and Gomorrah as one of five cities of that plain, always named next after Sodom. It says those cities probably stood close together near the northern end of what is now the Dead Sea, and that no trace of Sodom or the other cities of the plain has been found.Sources: the Bible text itself · Sodom · Gomorrah
  • The chapter says these false teachers left the straight way to follow Balaam son of Beor, who loved the wages of wickedness and was rebuked by a donkey, otherwise without speech, that spoke with a human voice. Easton's Bible Dictionary describes Balaam as a man of some rank among the Midianites who lived at Pethor in Mesopotamia; though he dwelt among idolaters, he had some knowledge of the true God, and Balak sent for him to curse Israel. The same dictionary notes that Beor, Balaam's father, is called Bosor in 2 Peter 2:15.Sources: the Bible text itself · Balaam · Beor
  • 2 Peter calls Noah a preacher of righteousness and says he was preserved among eight people when the flood came on the ungodly of the ancient world. Easton's Bible Dictionary identifies him as the son of Lamech and the grandson of Methuselah, and describes him as a link between the old world and the new and as the second great progenitor of the human family. It records that he lived five hundred years before his three sons, Shem, Ham, and Japheth, were born.Sources: the Bible text itself · Noah

Notes written with AI assistance from open sources (Theographic Bible Metadata, CC BY-SA 4.0; Easton’s Bible Dictionary, public domain) and reviewed before publishing.

Credits and license for this translation
መጽሐፍ ቅዱስ
The New Testament in the Amharic language of Ethiopia
copyright © 1962, 2003 United Bible Societies
Language: አማርኛ (Amharic)
Amharic NT
Revised Amharic Bible in XML (2003).
Printed version by United Bible Societies (C)1962.
E-Text in transliterated ASCII format by Lapsley/Brooks Foundation 1994.
Unicode UTF-8 transformation and XML-tagging by Dirk Röckmann 2003 ( www.nt-text.net ).
With kind permission of the Bible Society of Ethiopia.
Every non-commercial work using this data in any form must fully include this copyright statement!
Every commercial use of parts or the complete data in any form needs written permission of the Bible Society of Ethiopia!
2014-09-09

Source: http://ebible.org/amh/ · eBible.org

Talk to us

Tell us where you read from, how the Bible has helped you, or what we could improve. We read every message.